Ethio Family Health Online Information Service

Directions Website

Ethio Family Health Online Information Service EFHOI delivers simple, reliable health education and interactive learning for the community.

🇫🇮 ፊንላንድ አሁንም ደስተኛ ነች😄ኢትዮጵያ ገና ነችለ ተከታታይ 8ኛ እመት በደስታ መለኪያ ምዘና አብዛኛው የፊንላንድ ህዝብ ደስተኛ እንደሆነ ታይቷል፡፡ ቁልፍ ምንጭ ተብለው የተገኙት (The...
26/07/2026

🇫🇮 ፊንላንድ አሁንም ደስተኛ ነች😄
ኢትዮጵያ ገና ነች

ለ ተከታታይ 8ኛ እመት በደስታ መለኪያ ምዘና አብዛኛው የፊንላንድ ህዝብ ደስተኛ እንደሆነ ታይቷል፡፡
ቁልፍ ምንጭ ተብለው የተገኙት (The right conditions)በ 4 ዋና ርዕስ እንደሚከተለው ይመስላል፡፡

👉እርስ በርስ በህዝብ (በማህበረሰብ) ዘንድ ያለ መተማመን (trust among people and on society)
👉ህዝብ መንግስት ላይ ያለው አመኔታ (trust in institutions)
👉ዝቅተኛ የሙስና መጠን
👉ተመሳሳይ (እኩል) እድል

የነዚህ ምክንያቶች መኖር ብቻውን ግን በቂ አልነበረም፡፡ በተጨማሪ ህዝቡ
ጽናት፤ ጥንካሬ፤ የመቋቋም ችሎታ እና ባለው (በተሰጠው) ልክ አውጥቶ በመጠቀም የለኝም የሚል አስተሳሰብን የሚቃወም
በመሆኑ ነው፡፡

⚖ሌላው ማንኛውም ግለሰብ ስለ ራሱ አኗኗር በራሱ የፈለገውን ውሳኔ የመወሰን ነጻነት (መብት) መጠቀም ልምድ መኖሩ በብዛት ተጠቅሷል፡፡ የ መንግስትም ሆነ ማህበረሰብ ወግ እና ህግጋት ግለሰብን መብት ጠብቀው ተጠቃሚ ለማድረግ የተመቻቹ ናቸው ማለት ነው፡፡

🌴ተፈጥሮን መውደድ እና በእለት ተዕለት ኑሮ ያላቸው ቁርኝት ደስታን እንደሚፈጥርላቸውም ሪፖርቱ ገልጷል፡፡

🇪🇹ኢትዮጲያ በሪፖርቱ 132ኛ ስትሆን አፍጋኒስታን ከኢትዮጵያ በ15 ደረጃ ዝቅ ብላ የመጨረሻ 147ኛ ደስተኛ ያልሆነች ሀገር ተብላለች፡፡

ምንጭ፡ UN world population review 2026 (July)
ሌሎች ተያይዞ የተገለፀ የሪፖርቱ አካሎች ለማንበብ በ
www.efhoi.com ይጎብኙ
Happiness Heroes

የተከበረ ሕይወት ከልመና ይበልጣል (Dignity over Begging)በበሽታ ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት ሰዎች በመንገድ ላይ ሲለምኑ ማየት እንደ ትክክለኛ ነገር ልንቀበለው አይገባም።ሕመም...
22/02/2026

የተከበረ ሕይወት ከልመና ይበልጣል (Dignity over Begging)

በበሽታ ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት ሰዎች በመንገድ ላይ ሲለምኑ ማየት እንደ ትክክለኛ ነገር ልንቀበለው አይገባም።

ሕመምምተኛ ወደ ሕክምና ሊመራ ይገባል። አካል ጉዳተኛም ወደ ተሃድሶ፣ ድጋፍ እና የሥራ ዕድል እንጂ በመንገድ ላይ ወደ የዕድሜ ልክ ኑሮ እና ልመና ሊያመራ አይገባም።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ማንኛውም ሰው ሰብአዊ ክብር፣ የጤና አገልግሎት ማግኘት እና ራሱን ችሎ የመኖር ዕድል ሊኖረው ይገባል። ሰዎች ባልታከመ ሕመም ምክንያት በድህነት ተገፋፍተው ለመለመን ሲገደዱ፣ ይህ የግለሰቡ ችግር ብቻ ሳይሆን የጤና እና የማህበራዊ ሥርዓቶቻችን መጠናከር እንዳለባቸው የሚያሳይ ምልክት ነው።
በእኛ ሀገር ደግሞ በሽታን መለመኛ ማድረግ የተለመደ ነገር ነው:: በአደባባይ የእግር ቁስል ; የቆዳ በሽታ ; የሽንት ቱቦ የያዙ እና የማይድኑ በሽታዎችን ወዘተ ያለባቸው አካላቸውን በማሳየት ከእግረኛ በርህራሄ ገንዘብ ይለምናሉ::
እውነተኛ ርኅራኄ ሳንቲም በመወርወር ብቻ አይገለጽም። እውነተኛ ርኅራኄ ማለት ሰዎች ዳግም እንዲቋቋሙ የሚያስችሉ የሕክምና፣ የተሃድሶ፣ የመጠለያ እና የሥራ ዕድሎችን መደገፍ ነው።

በመንገድ ላይ በሕመም የታጀበ ኑሮ እንዲያበቃ፤ ለክብር፣ ለሕክምና እና ለተስፋ በጋራ እንቁም!

www.efhoi.com
ይጎብኙን


27/01/2026

ያልታቀደ እርግዝና ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
- የእርግዝና መከላከያ መድሀኒት (ኮንዶም) አለማግኘት
- የአዕምሮ ጤና ችግር
- የጾታ አጋር ጫና
- የማህበራዊ ድጋፍ ማጣት
በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው::

አንዲት ሴት ያልታሰበ እርግዝና ሲያጋጥማት ምን ማድረግ እንዳለባት ለመወሰን ስትቸገር ወይም የተሳሳተ ውሳኔ ስትወስን ይስተዋላል::

ነገር ግን ይህ ክስተት የተለመደ እና ሌላም ሰው ላይ የሚከሰት መሆኑን በመረዳት ቀጣይ ውሳኔሽን በአስተውሎት ማድረግ ይኖርብሻል::

የበለጠ መረጃ በድረ ገጻችሁ www.efhoi.com ያገኛሉ::

EFHOI Online Health Information Service is a web-based platform dedicated to providing essential educational content on common health topics with public health significance.

Address

Arada Sub-city
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Family Health Online Information Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share