28/07/2026
የዓለም የሄፓታይተስ ቀን
የዘንድሮው የዓለም የሄፓታይተስ ቀን መሪ ቃል "ሄፒታይተስ፡ እንሰባብረው" የሚል ሲሆን፣ ዋና ዓላማው ስለ ቫይረሱ መተላለፊያ፣ ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ ነው።
ማወቅ ያለብን መሠረታዊ እውነታዎች፦
• ዝምተኛው ገዳይ፦ ሄፓታይተስ ቢ (HBV) እና ሄፓታይተስ ሲ (HCV) ለዓመታት ምንም ዓይነት የሕመም
ምልክት ሳያሳዩ በሰውነታችን ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ። ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት ጉበታችን በከፍተኛ ሁኔታ
ከተጎዳ በኋላ ነው።
• የበሽታው ደረጃዎች፦ ቫይረሱ በጊዜ ካልተገኘና ካልታከመ ቀስ በቀስ የጉበት ጠባሳ (Cirrhosis)፣ በመቀጠልም
ወደ ጉበት ካንሰር (HCC) ሊቀየር ይችላል።
• የላቦራቶሪ ምርመራ አስፈላጊነት፦ ቫይረሱ በደማችን ውስጥ መኖሩን ማወቅ የሚቻለው በምርመራ ብቻ ነው።
በተጨማሪም የቫይረሱን መጠን (Viral Load) በየጊዜው መለካት በሽታው እንዳይባባስ ለመቆጣጠር
ይረዳል።ኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላቦራቶሪስ
ለጉበት ጤና አስፈላጊ የሆኑትን የሄፓታይተስ የደም ምርመራዎች፣ የቫይረስ መጠን መለኪያ እና የላቁ ካንሰር ጠቋሚ ምርመራዎች በሁሉም ቅርንጫፎቹ እና የናሙና መቀበያ ማዕከላት (CSCs) ያከናውናል። ጤናዎን አስቀድመው ይጠብቁ!
This World Hepatitis Day, the global medical community is focused on breaking down the complexities of viral hepatitis to improve public understanding, prevention, and early management.
The Clinical Progression: What You Need to Know
• The Silent Phase: Hepatitis B (HBV) and Hepatitis C (HCV) routinely replicate
in the body for decades without causing pain, jaundice, or physical symptoms.
• From Inflammation to Malignancy: Left unmanaged, chronic viral replication
drives continuous liver necroinflammation. Over time, this healthy tissue is
replaced by permanent scarring (cirrhosis), which dramatically elevates the risk
of developing Hepatocellular Carcinoma (HCC/Liver Cancer).
• Tracking Viral Load: Molecular PCR testing is used to measure the exact
amount of virus in the blood. This helps clinicians evaluate if the virus is
actively damaging the liver or if antiviral treatments are successfully keeping it
suppressed.
To support preventive screening and comprehensive liver care, International Clinical Laboratories (ICL) offers high-precision Hepatitis serology, quantitative PCR viral loads, and advanced automated PIVKA-II testing across our entire network of branches and local Collection Service Centers (CSCs).