Bethesda American Medical Plaza

Bethesda American Medical Plaza Ethiopia’s First and Only Medical Plaza — Your One-Stop Destination for Comprehensive Healthcare. Visit us today!

Discover a new standard of care, where all your medical needs are met under one roof.

16/06/2026

ስለ ማታ ላብ (Night Sweats) ማወቅ ያለባችሁ ነገ

15/06/2026

🧂 Always reaching for extra salt?
Excessive salt cravings can sometimes signal an underlying health issue.

የፊንጢጣ ኪንታሮት (Hemorrhoids) ምንድን ነው?የፊንጢጣ ኪንታሮት በፊንጢጣ አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች (Veins) ከልክ በላይ ሲያብጡ እና ሲለጠጡ የሚከሰት የጤና እክል ነው። በማን...
13/06/2026

የፊንጢጣ ኪንታሮት (Hemorrhoids) ምንድን ነው?
የፊንጢጣ ኪንታሮት በፊንጢጣ አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች (Veins) ከልክ በላይ ሲያብጡ እና ሲለጠጡ የሚከሰት የጤና እክል ነው። በማንኛውም የእድሜ ክልል ላይ ሊከሰት ቢችልም፣ በተለይ ከ45 እስከ 65 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ማህበረሰቦች ላይ በስፋት ይስተዋላል።

🔄
የኪንታሮት ዓይነቶች
የፊንጢጣ ኪንታሮት በዋናነት በሁለት ይከፈላል፦
🔴 ውጫዊ ኪንታሮት (External Hemorrhoids)፦ በውጨኛው የፊንጢጣ ቆዳ ስር የሚከሰት ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የሕመም ስሜት፣ እብጠት እና ማሳከክ ያስከትላል።
🔵 ውስጣዊ ኪንታሮት (Internal Hemorrhoids)፦ በፊንጢጣ ውስጠኛው ክፍል ላይ የሚከሰት ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ ህመም የለውም። ነገር ግን እንደየእድገቱ ደረጃ በሚከተሉት አራት ደረጃዎች (Grades) ይከፈላል፦
ደረጃ 1፦ እብጠቱ በፊንጢጣ ውስጠኛው ግድግዳ ላይ ብቻ የሚገኝ ሲሆን፣ ወደ ውጭ አይወጣም።
ደረጃ 2፦ በሰገራ ወቅት በሚኖር ግፊት (ማማጥ) ምክንያት እባጩ ወደ ውጭ ይወጣል፤ ነገር ግን ሰገራ ከተጠናቀቀ በኋላ በራሱ ጊዜ ወደ ውስጥ ይመለሳል።
ደረጃ 3፦ እባጩ ወደ ውጭ ይወጣል፣ በራሱ ጊዜ ስለማይመለስ በእጅ በመግፋት ወደ ውስጥ መመለስን ይሻል።
ደረጃ 4፦ እባጩ ሙሉ በሙሉ ወደ ውጭ ወጥቶ የሚቀር እና በእጅ እንኳ ወደ ውስጥ መመለስ የማይቻልበት የመጨረሻው ደረጃ ነው።

⚠️
አጋላጭ ሁኔታዎች (Risk Factors)
❇️ የሆድ ድርቀት
❇️ እርግዝና
❇️ የትልቁ አንጀት ካንሰር
❇️ ሽንት ቤት ተቀምጦ ለረጅም ጊዜ ማማጥ
❇️ ረጅም ጊዜ የቆዬ ተቅማጥ (Chronic diarrhea)
❇️ ዕድሜ መጨመር

☎️ 6737/ 0998014543 / 0998084543

📍አድራሻ:- 22 ካፒታል ሆቴል ፊትለፊት ከሉሲ ኢንሹራንስ አጠገብ


(https://web.facebook.com/watch/hashtag/internationalhospital/?__cft__[0]=AZaH9YghKkTH9hsgBKgSxolBGyjxf0X7WnfCp_IKfiy3TU9ZWloRR9eXswz4c0op2CIWOawYPRL0T8y0R1fPVlrrM_FbmqjLVJxR3xl0lH8aEFhnabNkjK7lA7P48NAA7menFjLKCxZGGe6uzshn_BbdBuL4O4xDEw_j-UaSIoc8VWc68X_UXY7x1Edw9k_tdn4DxJD7yrYYnpoSPnIUiaY-&__tn__=*NK-R)

አክታ ለይ ደም መቀላቀል በምን ይፈጠራል?1. እንደ ሳንባ ምች ባሉ የሳንባ ኢንፌክሽኖች 2. የሳንባ ቲቢ 3. የሳንባ ቱቦ በሚሰፋበት ወቅት/ ብሮንኬክታሲስ 4. በሳንባ ካንሰር 5. በሳንባ ...
11/06/2026

አክታ ለይ ደም መቀላቀል በምን ይፈጠራል?

1. እንደ ሳንባ ምች ባሉ የሳንባ ኢንፌክሽኖች
2. የሳንባ ቲቢ
3. የሳንባ ቱቦ በሚሰፋበት ወቅት/ ብሮንኬክታሲስ
4. በሳንባ ካንሰር
5. በሳንባ ውስጥ ደም ሲረጋ

በእነዚህ ምክኒያቶች አክታ ላይ ደም የመቀላቀል ምልክት ሊኖር ይችላል፡፡ ታድያ ይህ ምልክት ችላ ባለማለት ቶሎ ህክምና ማግኘትን ይፈልጋል፡፡
የተሟላ የሳንባ ህመሞች ህክምናን በቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ ማግኘት ይችላሉ፡፡

☎️ 6737/ 0998014543 / 0998084543

📍አድራሻ:- 22 ካፒታል ሆቴል ፊትለፊት ከሉሲ ኢንሹራንስ አጠገብ


09/06/2026

Birth control pills don’t directly create gallstones overnight, but their hormones can increase cholesterol in bile and slow gallbladder emptying—making gallstones more likely in some women.

የትልቅ አንጀት ካንሰር ምልክቶች ምንድን ናቸው?1. ሰገራ ለይ ደም መቀላቀል 2. የሆድ ድርቀት / የማስቀመጥ ምልክት 3. ሽንት ቤት ስትጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የጨረሳቹ ያህል ያለመሰማት ስሜት 4...
08/06/2026

የትልቅ አንጀት ካንሰር ምልክቶች ምንድን ናቸው?

1. ሰገራ ለይ ደም መቀላቀል
2. የሆድ ድርቀት / የማስቀመጥ ምልክት
3. ሽንት ቤት ስትጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የጨረሳቹ ያህል ያለመሰማት ስሜት
4. የሆድ ህመም/ ቁርጠት
5. ሆድ መነፋት/ ጋዝ የመብዛት
6. የሰውነት ክብደት መቀነስ ምልክቶች የትልቅ አንጀት ካንሰር በሚኖርበት ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው፡፡

ሙሉ የአንጀት ህመሞች ህክምና በቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ ማግኘት ይችላሉ፡፡
☎️ 6737/ 0998014543 / 0998084543

📍አድራሻ:- 22 ካፒታል ሆቴል ፊትለፊት ከሉሲ ኢንሹራንስ አጠገብ


በቤቴስዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ (BAMP)፣ ለቅድመ-መከላከል ያለን ቁርጠኝነት ከሆስፒታላችን ቅጥር ግቢ በላይ ይዘልቃል። ታዋቂው  በሸራተን አዲስ ሆቴል (Sheraton Addis, a Lux...
08/06/2026

በቤቴስዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ (BAMP)፣ ለቅድመ-መከላከል ያለን ቁርጠኝነት ከሆስፒታላችን ቅጥር ግቢ በላይ ይዘልቃል። ታዋቂው በሸራተን አዲስ ሆቴል (Sheraton Addis, a Luxury Collection Hotel) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ልዩ የጤና ዘመቻ ላይ የጤና ክትትል በማድረጋችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል።
በዚህ ለየት ባለ መርሃ-ግብር ላይ፣ የላቀ ብቃት ያለው የህክምና ቡድናችን ለሆቴሉ ሰራተኞች የደም ግፊት ልኬት እና የስኳር በሽታ ምርመራ አድርጓል። በሽታን አስቀድሞ መለየት ለረጅም ዕድሜ እና ለጤማ ህይወት መሠረት ነው
ጤናማ ማህበረሰብን ባት ከእኛ ጋር አብሮ በመስራቱ ለሸራተን አዲስ ቡድን ምስጋናችንን እናቀርባለን።

☎️ 6737/ 0998014543 / 0998084543

📍አድራሻ:- 22 ካፒታል ሆቴል ፊትለፊት ከሉሲ ኢንሹራንስ አጠገብ


ችላ መባል የሌለባቸው የራስ ህመም ዓይነቶች 1. እንደጀመረ ቶሎ የሚባባስ የራስ ህመም ስሜት 2. ከህመሙ ጋር የሰውነት ክፍል መድከም፤ ግራ መጋባት እና ማውራት መቸገር ምክልት ካለ 3. ከህ...
05/06/2026

ችላ መባል የሌለባቸው የራስ ህመም ዓይነቶች

1. እንደጀመረ ቶሎ የሚባባስ የራስ ህመም ስሜት
2. ከህመሙ ጋር የሰውነት ክፍል መድከም፤ ግራ መጋባት እና ማውራት መቸገር ምክልት ካለ
3. ከህመሙ ጋር የሰውነት ትኩሳት እና የአንገት መገተር ምልክት ካለ
4. ከህመሙ ጋር የሰውነት መንቀጥቀጥ/ የመጣል ምልክት ካለ
5. ጠዋት ጠዋት የሚባባስ የራስ ህመም ከሆነ በተለይም ወደላይ የማለት ምልክት ካለ ቶሎ ህክምና ማግኘት አስፈላጊ ነው፡፡

☎️ 6737/ 0998014543 / 0998084543

📍አድራሻ:- 22 ካፒታል ሆቴል ፊትለፊት ከሉሲ ኢንሹራንስ አጠገብ

04/06/2026

Cold weather doesn’t cause pneumonia—germs do. ❄️🦠 Don’t blame the weather; protect yourself from infections and stay informed!

🦶💥ሪህ (Gouty Arthritis) ምንድን ነው?💥🦶ሪህ የመገጣጠምያ ህመም ሲሆን በደም ውስጥ ከመጠን በላይ የዩሪክ አሲድ መከማቸት ምክንያት ይመጣል። ዩሪክ አሲድ ሲከማች እንደ መርፌ የሚወ...
02/06/2026

🦶💥ሪህ (Gouty Arthritis) ምንድን ነው?💥🦶

ሪህ የመገጣጠምያ ህመም ሲሆን በደም ውስጥ ከመጠን በላይ የዩሪክ አሲድ መከማቸት ምክንያት ይመጣል። ዩሪክ አሲድ ሲከማች እንደ መርፌ የሚወጉ ጥቃቅን ክርስታሎች ( ድንጋዮችን) በመገጣጠሚያ ውስጥ ይፈጠራሉ። ሪህ በብዛት መነሻው የሚያደርገው በእግር አውራ ጣት ላይ ነው

🔹 ዋና ዋና ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

✅ድንገተኛ ከባድ የመገጣጠሚያ ህመም ( በብዛት ማታ ማታ )
✅የመገጣጠሚያ እብጠት, መቅላት እና ማተኮስ
✅ የእንቅስቃሴ መገደብ
በከፍተኛ በከፍተኛ ህመም ምክንያት እግርን ለማንቀሳቀስ ወይም ለመርገጥ መቸገር
✅በአንድ መገጣጠሚያ (በብዛት የእግር አውራጣት፣ ጉልበት ወይም ቁርጭምጭሚት) የሚጀምር ህመም ሊያሳይ ይችላል።

🔹ሪህ በምን ሊቀሰቀስ ይችላል?

🍖 ቀይ ስጋ ወይም የባህር ምግቦች (sea foods)
🍺 አልኮል መጠጦች በተለይም ቢራ
🥤 ስኳር የበዛባቸው መጠጦች እና
💊 በጣም የሚያሸኑ መድኃኒቶችን መጠቀም ሪህን ሊቀሰቅሰው ይችላል

🔹 ሪህን እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?

✅የታዘዘውን መድሃኒት በአግባቡ መውሰድ
✅ውሃ በደንብ መጠጣት
✅የሚቀሰቅሱ ምግቦችን አለመውሰድ
✅አልኮል እና ስኳራማ መጠጦችን አለመውሰድ እና
✅ክብደትን መቆጣጠር ሪህን ለመቆጣጠር ይረዳል።

📌 የተጠቀሱትን ምልክቶች ካዩ ወደ ሆስፒታላችን በመምጣት ተገቢውን ምርመራ እና ህክምና በስመጥር ስፔሻሊስት ሐኪሞቻችን ያግኙ።

📍አድራሻ፡- 22 ካፒታል ሆቴል ፊትለፊት ከሉሲ ኢንሹራንስ አጠገብ

ቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ
ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ እንክብካቤ !

Address

22 Opposite Of Capital Hotel, Next To Lucy Insurance
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bethesda American Medical Plaza posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category