21/08/2026
አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እያከውናቸው ከሚገኙ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች አካል የሆነ ‘በጎ አድራጎት ለጤናማ ማህበረሰብ’ በሚል መሪ ቃል በቀን 14/12/18 ዓ.ም የደም ግፊት፤ የስኳር የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር፤ የHIV AIDS፤ የቲቢ ፣የአይን ምርመራ ዘመቻ እንዲሁም በርኆቦት የበጎ አድራጎት ድርጅት በመገኘት የህክምና ድጋፍ አከናውኗል።
በሆስፒታሉ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም በተመራው በጎ አድራጎት፣ የዕድገት ክትትል፣ ስር የሰደደ ሕመም፣የአጥንት ችግር ፣ በአይረን እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ ፣አካል ጉዳተኝነት እንዲሁም ከውልደት የመጣ የአፈጣጠር ችግር የምርመራና የህክምና አገልግሎት በበጎ አድራጐት ተቋሙ ተጠልለው ላሉ ህፃናት ተደርጐላቸዋል።
እንዲሁም በታቦር ክፍለከተማ ፋራ ቀበሌ አዲሱ መናሀሪያ አካባቢ በተካሄደው ዘመቻ በርካታ የማህበረሰብ ከፍል አገልግሎት ያገኘ ሲሆን መርሀግብሩም በተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶች ታጅቦ ውሏል።