Panacea Hospital - ፓነሲያ ሆስፒታል - Hawassa

Panacea Hospital - ፓነሲያ ሆስፒታል - Hawassa Panacea Hospital is Hub of more than 20 Specialists and Subspecialists

ፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ ከ20 በላይ ስፔሻሊስቶች እና ሰብ-ስፔሻሊስቶች መገኛ ማዕከል በፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ በቀን 13/03/2018 ዓ/ም  በምስሉ የተገለፀውን የሀሞት ከረጢት ጠጠር...
23/11/2025

ፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ
ከ20 በላይ ስፔሻሊስቶች እና ሰብ-ስፔሻሊስቶች መገኛ ማዕከል

በፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ በቀን 13/03/2018 ዓ/ም በምስሉ የተገለፀውን የሀሞት ከረጢት ጠጠር በቀዶ ህክምና ከአንዲት ሴት ታካሚያችን በሆስፒታሉ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት በዶ/ር ፀጋዬ ቸቦ እና በዕለቱ ቀዶ ህክምና ቡድን አማካኝነት በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

የታካሚያችንን ቀዶ ህክምና ከባድና ውስብስብ ያደረገው ጉዳይ ፦ ታካሚያችን አጣዳፊ የሆነ የሀሞት ጠጠር ህመም ወይም ቁስለት (Acute cholecystitis) እና የሀሞት ከረጢት ከመጠን በላይ በፈሳሽ መወጠርና ማበጥ ( Gallbladder Hydrops) የነበረባቸው በመሆኑ ነው።

Cholecystectomy - የሃሞት ከረጢት ጠጠር ኦፕሬሽን
ቀላል ነው ወይስ ከባድ?

👉 ብዙውን ጊዜ "የተለመደ ህክምና" ነው፣ ሂደቱም ቀላል ነው ተብሎ ይታመናል። ይሁን እንጅ - የተለመደ ነው ማለት በኦፕራሲዮን ጊዜ ከአደጋ ነፃ ነው ማለት አይደለም።

👉 Cholecystectomy / የሀሞት ከረጢት ጠጠር ቀዶ ህክምና ቀላል የሚሆነው መቼ ነው?

✔ታካሚው ያለው የሰውነት አወቃቀር (Anatomy) ግልጽ እና ቀጥተኛ ሲሆን የቀዶ ህክምና ሂደት ውስብስብነት ይቀንሳል።
✔የሃሞት ከረጢቱ ተደጋጋሚ ጉዳት (chronic cholecystitis) የሌለው ሲሆን እና አጣዳፊ የሆነ የሀሞት ጠጠር ሕመም ወይም ቁስለት (Acute cholecystitis) ከሌለ።
✔ህክምናው ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቀዶ ህክምናውን ጊዜ እና ውስብስብነትን ይቀንሳ።

👉 Cholecystectomy/የሀሞት ከረጢት ጠጠር ቀዶ ህክምና አስቸጋሪ የሚያደርገው ምንድን ነው?

✔ከባድ እና ተደጋጋሚ ቁስለት (Chronic cholecystitis with contracted gallbladder)፡ በተለይም ሥር በሰደደ የሀሞት ከረጢት ኢንፌክሽን ወይም ቀደም ባሉት የሀሞት ኢንፌክሽኖች ሲከሰት የቀዶ ህክምናው ውስብስብነት ይጨምራል።
✔ከተለመደው የተለየ አፈጣጠር (Anatomic Variation) ፡ በሀሞት ቱቦ ወይም ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ላይ ያለው አቀማመጥ ልዩነት ሊኖር ይችላል፣ ብዙ ጊዜም የሚገጥም ነገር ነው። የዚህ ችግር ያለባቸው ሰዎችንም ቀላል በሆኑ እና በተለመዱት የምርመራ ዘደዎች መለየት አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ በኦፕራሲዮን ጊዜ ሊገጥም እንደሚችል መገመት እና ሲገጥምም ተገቢውን ህክምና ማድረግ ያስፈልጋል። ካልሆነ ግን የኦፕራሲዮኑን ሂደት እና የማገገም ሂደቱን ውስብስብ ያደርጉዋል።

✔ከመጠን ያለፈ ውፍረት (Morbid Obesity) ፡ ከመጠን ያለፈ ውፍረት በኦፕራሲዮን ጊዜ እይታን ይጋርዳል። ይህ መሆኑ ደግሞ ይሂደቱን ውስብስብነት እና በኦፕራሲዮን ጊዜ የሚደርስን አደጋ ይጨምራል። በዚህኛውም አጋጣሚ ኦፕራሲዮኑን በቀነሰ የአደጋ ተጋላጭነት ለመከወን ልምድ ይፈልጋል።
👉ሂደቱን ቀላል ለማድረግ፣
✔ በኦፕራሲዮን ጊዜ አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት መርሆችን (Safety principles) መተግበር ያስፈልጋል።
✔እርዳታ መጠየቅ፡ በኦፕራሲዮን ጊዜ ሁለተኛ አስተያየት ከሌላ ባለሙያ መጠየቅ ውጤቱን ያማረ ሊያደርገው ይችላል።
✔በአጠቃላይ ከታካሚ ምርጫ ጅምሮ በጥንቃቄ ነገሮችን ማየት በሃሞት ከረጢት ጠጠር ኦፕራሲዪን (Cholecystectomy) ወቅት ሊገጥም የሚችልን ውስብስብነት እና አደጋ ይቀንሳል።
በመጨረሻም፦
✔ የሀሞት ጠጠር ምልክቶች ምንድን ናቸው??
አብዛኞቹ የሀሞት ጠጠሮች በጊዜ ምልክት የማያሳዩ ሲሆን በአብዛኛው ጊዜ ቅባታማ ምግቦችን ከተመገቡ በሗላ የምከሰት እና የሚታዩት ምልክቶች የሚከተሉት ናቸዉ ፦
※ ለረጅም ሰዓት የሚቆይ በሆድ የላይኛው ቀኝ ክፍል ድንገተኛ የመውጋትና የማቃጠል ህመም
※ በቀኝ ትከሻ ላይና በትከሻ መሳቢያዎች መካከል የጀርባ ህመም
※ ማቅለሽለሽ
※ ማስመለስ
※ ምግብ ያለመፈጨት ችግሮች
※ የሆድ መነፋት፣ ቃር፣ ማቃጠል እና ጋዝ የመሳሰሉትን ናቸው።
ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩ ምልክቶች ካለዎት ይህ የሀሞት ከረጢት ጠጠር ህመም ( Symptomatic Cholelithiasis) ምልክት ሊሆን ስለምችል ባፋጣኝ ወደ ፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ ይምጡ ፤ በሆስፒታላችን መፍትሄ ያገኛሉ፡፡

✍️ በዶ/ር ፀጋዬ ቸቦ: የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት
Dr. Tsegaye Chebo, MD, General Surgeon

ፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ
ከ20 በላይ ስፔሻሊስቶች እና ሰብ-ስፔሻሊስቶች መገኛ ማዕከል

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ +251994191919 / 0462124243 ላይ ይደውሉልን!

አድራሻ ፦ ሀዋሳ ወደ ሪፈራል ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ላይ ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ያገኙናል።

የኩላሊት ፣ የሽንት ቱቦ ፣ የፊኛ እና የፕሮስቴት ከፍተኛ ቀዶ ህክምና በሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም በፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ ዶ/ር ጥላነህ ልይህየኩላሊት ፣ ሽንት ፊኛ እና ፕሮስቴት ቀዶ ህክም...
03/12/2024

የኩላሊት ፣ የሽንት ቱቦ ፣ የፊኛ እና የፕሮስቴት ከፍተኛ ቀዶ ህክምና በሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም በፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ

ዶ/ር ጥላነህ ልይህ
የኩላሊት ፣ ሽንት ፊኛ እና ፕሮስቴት ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪምን በፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ ያገኙዋቸዋል፡፡
Dr. Tilaneh Leyeh - General surgeon, Urologist - Available at Panacea Hospital Hawassa.

ፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ
ከ20 በላይ ስፔሻሊስቶች እና ሰብ-ስፔሻሊስቶች መገኛ ማዕከል

1. የኩላሊት ጠጠር ምንድነው?

[ ] የኩላሊት ጠጠር ኩላሊት ውስጥ እና ሁሉም የሽንት ቱቦዎች ውስጥ የሚፈጠር ጠጣር ነገር ሲሆን ኩላሊትን በማቁሰል እና የሽንት ፈሰትን በመዝጋት ኩላሊትን ሙሉ በሙሉ እስከመጉዳት ሊያደርስ የሚችል የበሽታ ዓይነት ነው፡፡
[ ] የኩላሊት ጠጠር ዓለም ላይ ካለው የመከሰት እድል በበለጠ መጠን አካባቢያችን ላይ ይታያል፡፡ በስራ ወቅት ካለን ጥልቅ ምልከታ በመነሳት በሲዳማ ክልል በሚገኝ አንድ ወረዳ ውስጥ በተደረገው የማህበረሰብ አቀፍ የዳሰሳ ጥናት የኩላሊት ጠጠር ስርጭት ከ 30 በመቶ በላይ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

2. የኩላሊት ጠጠር ምልክቶች፡

• ኩላሊት አካባቢ የህመም ስሜት
• የሽንት ቀለም/ሽታ መቀየር፣ ሽንት ማቃጠል እና ቶሎ ቶሎ መምጣት
• የድካም ስሜትና ክብደት መቀነስ … ናቸው፡፡
ሆኖም የኩላሊት ጠጠር ሀኪም ቤት ለመሔድ የማያሰገድድ መጠነኛ ህመም ወይም ምንም ዓይነት ህመም ላይኖረው የሚችል ስለሆነ ወደ ሀኪም ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመጡ ኩላሊታቸው ላይ የማይመለስ ጉዳት ደርሶባቸው የምናገኛቸው ታካሚዎች ቁጥር ቀላል አይደለም ፡፡

3. የሚደረጉ ምርመራዎች

የኩላሊት ጠጠርን እና ጤንነትን ለማዬት የሶኖግራፊ እና ውስን የደም ምርመራዎች የሚደረጉ ሲሆን ሶኖግራፊ ላይ ጠጠር ከተገኘ እና ቀዶ ህክምና የሚያስፈልግ ከሆነ የሲ.ቲ እስካን ተጨማሪ ምርመራ ይሰራል፡፡

4. ለኩላሊት ጠጠር የሚሰጡ ህክምናዎች

• ክትትል ማድረግ -----ትንንሽ መጠንና ችግር ላልፈጠሩ ጠጠሮች
• በመድሀኒት የሚደረግ ህክምና ---- የሽንት ቱቦ ውስጥ የተገኙ እና በመድሀኒት እገዛ ሊወጡ የሚችሉ ጠጠሮች
• በቀዶ ህክምና ጠጠሮችን ማውጣት

🔴ማስገንዘቢያ🔴

ጠጠሩ ኩላሊት ላይ ሊመለስ የማይችል ጉዳት ካደረሰ እና የተጎዳው ኩላሊት ሰውነት ውስጥ መቆየቱ የህመምተኛውን ጤና የሚያውክ ሆኖ ከተገኜ ከጥቅም ውጭ የሆነውን ኩላሊት ማውጣት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

5. የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች፡

ሀ/ አመጋገብ፡
• የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል እና ለአጠቃላይ የሰውነት ጤንነትአትክልትና ፍራፍሬ አዘውትሮ መመገብ ይመከራል፡፡
• ጣፋጭ ምግቦችን፣ ከፈተኛ ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች (ምሳሌ - ስጋ) እና ጨው አብዝቶ መጠቀም እንዲሁም ሲጋራ ማጨስ ለኩላሊት ጠጠር አጋላጭ ያደርጋል፡፡
ለ/ ፈሳሽ አወሳሰድ፡
• የኩላሊት ጠጠር መፈጠር መንስዔ በሽንት ውስጥ ሟሙተው መወገድ ያለባቸው ኬሚካሎች ከሽንት መጠን በላይ ሲሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም የምንወስደው የፈሳሽ መጠን ሲጨምር የሽንት ብዛት ስለሚጨምር እነዚህ ኬሚካሎች ሟሙተው ስለሚወጡ ዝቃጭ/ጠጠር የመፍጠር እድል አይኖራቸውም ማለት ነው፡፡
• ፈሳሽ በተለያዬ መልክ መውሰድ የሚቻል ሲሆን የለስላሳ መጠጦችን አብዝቶ መጠቀም ግን አይመከርም፡፡

6. የኩላሊት ጠጠር በጊዜ ካልታከመ የሚያመጣው ችግር

• ተደጋጋሚ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን
• ጊዚያዊ የኩላሊት ስራ መስተጓጎል
• የማይመለስ የኩላሊት ጉዳት
• በረጅም ጊዜ የኩላሊት ካንሰር መፍጠር

7. የማጠቃለያ ምክር

1. ማንኛውም ሰው ለኩላሊት ጠጠር መከላከል እና ለአጠቃላይ ሰውነት ጤና ጠቃሚ የሆነ የአመጋገብ ስርዓት መከተልና በቂ ፈሳሽ (በቀን ከ2 እስከ 3 ሊትር ) መውሰድ ይገባል፡፡
2. መንኛውም ሰው የኩላሊቱን ጤንነትና የጠጠር መኖር/አለመኖር ቢያንስ አነድ ጊዜ ምርመራ ቢያደርግ ሳይታወቅ ከሚፈጠር የኩላሊት ጉዳት ራሱን ይጠብቃል፡፡
3. የኩላሊት ጠጠር የተገኘበት ሰው ጊዜ ሳያጠፋ አስፈላጊውን ህክምና እና ክትትል ሊያደርግ ይገባል፡፡

ፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ
ከ20 በላይ ስፔሻሊስቶች እና ሰብ-ስፔሻሊስቶች መገኛ ማዕከል

ዶ/ር ጥላነህ ልይህ
የኩላሊት ፣ ሽንት ፊኛ እና ፕሮስቴት ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪምን በፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ ያገኙዋቸዋል፡፡

በተጨማሪም ለማንኛውም ከቀላል እስከ ከባድ ውስብስብ ቀዶ ህክምናን በተመለከተ፦ ጥያቄ ፣ ምክር ፣ ቀጠሮ መያዝ እና ህክምና ማድረግ ካሻዎት በቀጥታ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪምን በአካል መጥተው ያግኙ ወይም

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ +251994191919 /+251957989898/ 0462124243 ላይ ይደውሉልን!!!

ፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ
ከ20 በላይ ስፔሻሊስቶች እና ሰብ-ስፔሻሊስቶች መገኛ ማዕከል

አድራሻ ፦ ሀዋሳ ወደ ሪፈራል ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ላይ ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ያገኙናል።

ጥራት ያለው አገልግሎት ለሁሉም !!!

Follow us on:
Youtube : https://youtube.com/
Telegram : https://t.me/panaceahospital

የኢንዶቬነስ ሌዘር ህክምና  - የቫሪኮስ ደም ስሮችን የሌዘር ቴክኖሎጂን በመጠቀም መዝጋት በፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳEndovenous Laser Ablation Treatment (EVLA): A ...
25/11/2024

የኢንዶቬነስ ሌዘር ህክምና - የቫሪኮስ ደም ስሮችን የሌዘር ቴክኖሎጂን በመጠቀም መዝጋት በፓነሲያ ሆስፒታል - ሀዋሳ

Endovenous Laser Ablation Treatment (EVLA): A Game-Changer In Varicose Vein Treatment at Panacea Hospital - Hawassa

Address

አድራሻ ፦ ሀዋሳ ወደ ሪፈራል ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ላይ ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት/Hawassa
Awassa
HAWASSA1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Panacea Hospital - ፓነሲያ ሆስፒታል - Hawassa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category