22/08/2022
የመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ከፍለው መታከም ለማይችሉ ዜጎች የክረምት በጎ ፍቃድ የነፃ ምርመራና ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው።
==========================
መካነ ሰላም፣ ነሀሴ 16/2014ዓ.ም (መካነ ሰላም ኮሙኒኬሽ) የመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት "በጎነት ለጤናችን" በሚል መሪ ቃል ከፍሎ የመታከም አቅም ለሌላቸው ዜጎች ከዛሬ ጀምሮ ለ6 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የነፃ ምርመራና ህክምና አገልግሎት በበጎ ፍቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች መስጠት ጀምሯል።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀሰን አሊ እንደገለፁት የክረምት በጎ ፍቃድ የነፃ ምርመራና ህክምና አገልግሎቱ አላማ በተለያዩ በሽታዎች እየተሰቃዩ ከፍሎ የመታከም አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ከስቃያቸው ለመታደግ፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለማህበረሰቡ የተጠናከረ ትምህረት ለመስጠትና ማህበረሰቡ ወደ ጤና ተቋም መጥቶ የመታከም ልምዱ እንድዳብር ለማድረግና ያለመ ነው ብለዋል።
በዚህ መሰረት በበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ በቢሊ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤ አሃድ ለ61 ነፍሰ ጡር እናቶች የአልትራሳውንድ ምርመራና የህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል ያሉት ስራስኪያጁ የደም ግፊት፣ የስኳር፣ የአይን እንድሁም የኤች አይቪ ምርመራና የህክምና አገልግሎትን ጨምሮ በዛሬው ዕለት 220 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በበጎ ፍቃደኛ ባለሙያዎች የነፃ ምርመራና ህክምና እንደተሠጠ ገልጸዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን ባለሙያዎቹ ተገቢውን አገልግሎት እንድሰጡ በህክም ባለሙያዎች የክሊኒካል ኦድት ስራ ሲሰራ መዋሉን ገልፀው ወደፊትም የማህበረሰባችንን የጤና ችግሮችን ለመፍታት ጥራት ያለውና ፍትሀዊ የሆነ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።
የመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒት የነርሶች ዳይሬክተር እና የቢኤስሲ ነርሲንግ ባለሙያ የሆኑት አማረ ጋሻው በበኩላቸው የሆስፒታሉ ባሙያወች አለ ምንም አስገዳጅነት በራሳቸው ተነሳሽነት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከፍሎ የመታከም አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የምርመራና የህክምና አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።
የምርመራና የህክምና አገልግሎቱ ሲደረግላቸው ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም በበኩላቸው የመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታ በነፃ በሰጣቸው የህክምና አገልግሎት መደሰታቸውን ገልፀዋል።
በመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል የክረምት በጎ ፍቃድ የምርመራና የህክምና አገልግሎቱ እስከ ነሀሴ 21/2014 ዓ.ም ድረስ ለስድስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።