02/04/2022
ወላጆች ለህፃናት ስለሚሰጡ ክትባቶች ምን ምን ማወቅ አለባቸው?
አንድ ህፃን አንድየተወለደለ/ች ከመልካም አመጋገብና አጠባበቅ ባሻገር በየጊዜው መወሰድ ያለበትን
ክትባቶች ወላጆች አሰታውሰው ማስከተብ እጅግ ጠቀሜታ አለው፡፡
ክትባት ማለት ለአንድ ለሚተላለፍ በሽታ መከላከያ አስቀድሞ የሚወሰድ መድሀኒት ሲሆን የሰውን የራሱን የመከላከል
አቅም በማዳበርና የመከላከያ ኬሚካሎች እንዲያመርት በማድረግ በሽታን ከመምጣቱ በፊት ይከላከላል፡፡
ክትባቶች በአመት ከ2-3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በበሽታ እንዳይያዙ ሲከላከል በበሽታው የተያዙ ሰዎች በአካባቢው
ቢኖሩ እንኳን ወደ ሰውነት ዘልቆ ገብቶ በሽታ እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡
የክትባት የጎንዮሽ ምልክቶች
አንድ ህፃን ክትባት ሲከተብ ከበሽታው ከራሱ የተሰራ መከላከያ በመሆኑ የጎንዮሽ አንዳንድ የማያሳስቡ ምልክቶች ሊኖሩ
ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ
መጠነኛ ትኩሳት
የተከተበበት ቦታ ማበጥ ሲነካ ማመም ቀይመሆን
መደካከም የምግብ ፍላጎት መቀነስ
ማስመለስ
ምናልባት የሚያሳስቡና በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም ሊያመጡ የሚገባቸው ምልክቶች
ማዞር እጅግ መደካከም
ማንቀጥቀጥ
ሰውነት ላይ ሽፍታ መውጣት
የፊት ጉሮሮ ጋር ማበጥ መተንፈስ መክበድ
የክትባት አሰጣጥ
ክትባቶች ብዙዎቹ በመርፌ መልክ በቆዳ የሚሰጡ ሲሆኑ አንዳንዶቹ በአፍ ጠብታ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
ክትባት የሚከላከላቸው 7 የህፃናት በሽታዎች
ዲፕቴሪያ(Diptheria)
ይህ በሽታ ወፍራም ፈሳሽ ጉሮሮ ውስጥ በማከማቸትና ሳንባን በማፈንና እንዲሁም ለመተንፈስ በመከልከል
የሚያጠቃ ካለታከሙ ለሞት የሚዳርግ በሽታ ነው፡፡
Tetanus (መንጋጋ ቆልፍ)
የሰውነትን ጡንቻ በተለይ የመንጋጋ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎችን በማጠንከር መተንፈስ እነዲከብዳቸው ያደርጋል፡፡
በመንጋጋ ቆልፍ ከሚያዙ 10 ህፃናት አንዱበሞት ይቀጠፋል፡፡
Pertusis (ትክትክ)
በጣም ከባድ የሆነ የማያቋርጥ ሀይለኛ ሳል ማስመለስ መተንፈስ እስኪከብድ ድረስ ሲኖር ትክትክ በሽታ ህፃኑ ሊኖርበት
ይችላል፡፡
Measles (ኩፍኝ) /mumps(ጆሮ ደግፍ)MMR
ኩፍኝና ጆሮ ደግፍ በቫይረስ የሚመጡ በሽታዎች ሲሆኑ የሰውነት ላይሽፍታዎችና ማሳከክ ሊኖር ይችላል፡፡ አንገት ስር
በግራና በቀኝ ከትኩሳትና ከህመም ጋር የተያያዘ እብጠት ሲኖር ደግሞ የጆሮ ደግፍ ምልክቶች
ናቸው እነዚህ በሽታዎች ብዙ ጊዜ ለህይወት የሚያሰጉ በሽታዎች ባይሆኑም ህፃናቶችን
እንዲሁም ትንንሽ ልጆችን ያሰቃያሉ፡፡
የህፃናት የሳንባ ምች (pnemocucus ,H.lnfluenza)Hib
አንድህፃን በተለይ ከ5 አመት በታች ሆኖ ራስምታት ሳልና የአተነፋፈስ ችግር ካለበት የሳንባምች በሽታ የተያዘ ሊሆን ይችላል
ይህንን አደገኛ በሽታ ለመከላከል የሚጠቅሙክትባቶችን ገና በልጅነቱ ካገኘ ግን ከነዚህ በሽታዎች ይጠበቃል፡፡
ሄቨታይተስ (hepatitis B)
የአይን ወይም የሰውነት ቢጫ መሆንና ተቅማጥ ማስመለስ መደካከም የጡንቻዎች የመገጣጠሚያ ወይም ሆድ ህመም የሄቨታይተስ
በሽታ በህፃናት ሲከሰቱ ከምናያቸው ምልክቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ፖሊዮ (polio) OPV
ይህ በሽታ በተለይ እንደኛ አይነት ሶስተኛ አለም አገራት የእግር አፈጣጠር ችግር ከሚያመጡ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በክትባት
መከላከል የሚቻል ክምድረገፅ ሊጠፋ የተቃረበ በሽታ ነው፡፡
የክትባት አሰጣጥ ጊዜ ፕሮግራም
BCG
(የሳንባ ነቀርሳ)
እንደተወለዱ
DPT
(ዲፕቴሪያ)
6፣10፣14 ሳምንት ላይ
(measles)
ኩፍኝ
9 ወር
ቫይታሚን A
በ6 ወር
አመት ከ3ወር ከዛ በየ6 ወር 5 አመትእስኪሞላ
ሮታ ቫይረስ
በ 45 ቀን ከዚያበወሩ(2ወር ከ15ቀን)
ቴታነስ (መንጋጋ ቆልፍ)
መጀመሪያበማንኛውምጊዜ
በ 3 አመቱ
በ 5አመቱ
በ 10 አመቱ
(MMR)
ኩፍኝና ጆሮ ደግፍ,ሩቤላ
አመት ከ3ወር
ሄፓታይተስ እና የሳንባምች
HepB፣ Hib
6፤10፤14 ሳምንት