College of Medicine and Health Sciences, Bahir Dar University, Ethiopia.

College of Medicine and Health Sciences, Bahir Dar University, Ethiopia. Welcome to the official FB page of Bahir Dar University College of Medicine and Health Sciences. The

ለመላው የኮሌጃችን ሰራተኞች ስብሰባ ጥሪየባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር መንገሻ አየነ እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮ...
21/09/2026

ለመላው የኮሌጃችን ሰራተኞች ስብሰባ ጥሪ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር መንገሻ አየነ እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከጠቅላላ የመምህራን፣ የጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውይይት ያካሂዳል።

በመሆኑም መላው የኮሌጃችን ሰራተኞች በስብሰባው ላይ እንድትገኙ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችኋል።

የስብሰባው አጀንዳዎች፡
1. የ2018 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
2. የ2019 ዓ.ም ዕቅድ
3. አጠቃላይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት

የስብሰባው ዝርዝር መረጃ፡

ቀን፡ መስከረም 21፣ 2019 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ
ቦታ፡ ጥበበ ግዮን ግቢ

ማስታወሻ፡

ስብሰባውን በታቀደው ሰዓት ለማጠናቀቅ እንድንችል ሁላችሁም በሰዓቱ እንድትገኙ አናሳስባለን።

  🔹🔹🔹🔹🔹ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ CSI (Children's Surgery International) ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከአሜሪካ ሀገር በሚመጡ ...
20/09/2026


🔹🔹🔹🔹🔹
ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ CSI (Children's Surgery International) ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከአሜሪካ ሀገር በሚመጡ ስፔሻሊስትና ሰብስፔሻሊስት ሀኪሞች ከጥቅምት 07/2019 እስከ 13/2019 ዓ.ም

🔸በአፈጣጠር ወይም በአደጋ ምክንያት ለተከሰተ የጆሮ ቅርፅ ችግር

🔸የከንፈርና የላንቃ ክፍተት (መሰንጠቅ) ችግር

🔸በተፈጥሮ ወይም በአደጋ ምክንያት የአፍንጫ መጣመም

🔸የአንገትና ፊት አካባቢ እብጠት፣ መጣመም ወይም ጠባሳና መሰል ችግር

ላለባቸው ታካሚዎች የነፃ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት ይሰጣል።

በመሆኑም ችግሩ ያለባችሁ ወገኖች የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እያልን በ07/02/2019 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:00 በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንድትገኙ እናሳስባለን።

ቀድሞ ወረፋ ለመያዝ ቢሮ ቂጥር 65 ዘወትር በስራ ሰዓት መመዝገብ ይችላሉ።

18/09/2026
የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገየባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ሸማቾች ማሕበር  ሰባታሚት  ከተማ ለሚገኙ 80  ተማሪዎች  82 ሺ ብር የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በዛሬው እለት ...
17/09/2026

የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ሸማቾች ማሕበር ሰባታሚት ከተማ ለሚገኙ 80 ተማሪዎች 82 ሺ ብር የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በዛሬው እለት አድርጓል።

የጥበበ ግዮን ሸማቾች ማሕበር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጌታቸው ስጦታው በበኩላቸው የማሕበሩ ዋና አላማ ለአባላቱ የኑሮ ውድነትን ጫና ለመቀነስ የእርሻ እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ እና አባላቱን ተጠቃሚ ማድረግ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቶ ጌታቸው አክለውም ማህበሩ ከመደበኛ ስራው በተጨማሪ ማሕበራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ በሸማች ማሕበሩ ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት ለማሕበራዊ አገልግሎት ድጋፍ ማረግ እንደሚገባ ያዝዛል፤ ያሉት ሊቀመንበሩ ይህንን ተከትሎ ለሰባታሚት ከተማና በአካባቢው ለሚኖሩ ከ80 በላይ አቅመ ደካማና ወላጅ አልባ ተማሪዎች ከ82 ሺ ብር በላይ ወጭ በማድረግ የደብተር፣ የአስክርቢቶ፣ የእርሳስ ፣መቅረጫ እና ላጲስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋ፡፡

በስነ-ስረዓቱ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ማኔጅግ ዳይሬክተር አቶ ምስጋናው ሙጨ ፣ የሰባታሚት ቀበሌ አስተዳዳሪዎች እና የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተገኝተው ለተማሪዎች የማነቃቂያ ንግግሮችን አድርገዋል፡፡ በዕለቱ ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች በኩላቸው በተደረገላቸው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደሰታቸውን እና ኮሌጁ ከሚሰጠው የሕክምና አገልግሎት በተጨማሪ የአካባቢውን ህብረተሰብ በትምህርት ቁሳቅስ በመደገፉ ኮሌጁን አመስግነው፤ ቀጣይ ያለምንም ሀሳብ ትምህርታቸው ላይ ብቻ አተኩረው እንዲማሩ እድል የፈጠረላቸው ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋ፡፡

Bahir Dar University Highlighted as Exemplar of French–Ethiopian Health Cooperation We are proud to share that Bahir Dar...
16/09/2026

Bahir Dar University Highlighted as Exemplar of French–Ethiopian Health Cooperation

We are proud to share that Bahir Dar University’s partnership with the University of Rennes—which established a reference laboratory for medical mycology in the Amhara Region—has been recognized by the Ambassade de France en Éthiopie et auprès de l'Union africaine as a successful model of international hospital and research cooperation!

https://www.facebook.com/share/19Wtg8AJry/

🇫🇷🇪🇹 The new edition of the International Hospital Cooperation Call for Projects (APCHI), supported by the French Ministry of Health (DGOS), is now open. Applications can be submitted until 28 September 2026 at midnight.

This initiative enables French healthcare institutions and professionals to share their expertise through international cooperation and solidarity.

French–Ethiopian health cooperation aims at promoting equitable and resilient health systems that ensure universal access to quality healthcare services, while strengthening preparedness and response to public health emergencies and the impacts of climate change through a One Health approach.

🤝 Recent examples of cooperation include:

1. Deployment of a reference laboratory for medical mycology in the Amhara Region, through a collaboration between the University of Rennes and Bahir Dar University.

2. Support for the Department of Obstetrics and Gynaecology at Jimma University, through the partnership and support of Claude Bernard University Lyon 1.

3. Establishment of urogynaecology teaching programmes

For more information about the APCHI Call for Projects and application procedures, please follow this link: https://sante.gouv.fr/professionnels/gerer-un-etablissement-de-sante-medico-social/cooperations/cooperation-hospitaliere-internationale-11333/cooperation-hospitaliere-internationale

Date: 15/09/2026G.C                                       CALLFOR APPLICATIONS  The Departmentof Internal Medicine invit...
15/09/2026

Date: 15/09/2026G.C

CALLFOR APPLICATIONS The Departmentof Internal Medicine invites qualified Internists to apply for the Pulmonologyand Critical
Care Medicine Fellowship P
rogram.Eligibility Requirements: • MD d
egree froma recognized university• Specialty
certificate in Internal Medicine• Licensed topractic
e Internal Medicine in Ethiopia• Minimum of 2years of ex
perience in Internal Medicine • Foreignapplicants must provide a letter of good standing and authe
nticatedprofessional license• Goo
d mentaland physical he
althRegistration Details: • Dat
es:September 15 - 30, 2026• Place:Department of Internal Medicine Office
/ office of the registrarFor online applications: [email protected] g
[email protected].
et Required
Documents: • Updated C
V• Specialtycertificate• Two
recommendation let
ters• NGATcertificate. Spons
orship/SupportletterOnly applicantsmeeting all eligibility criteria and submitting required documents will be considered.

Project HOPE Visit Tibebe Ghion Specialized Hospital to Review Laboratory Progress BAHIR DAR, ETHIOPIA, September 2026 —...
14/09/2026

Project HOPE Visit Tibebe Ghion Specialized Hospital to Review Laboratory Progress

BAHIR DAR, ETHIOPIA, September 2026 — Project Hope Representatives led by Dr. Wes Kim Director for Global Health Programs, American Society for Microbiology (ASM) and Dr. Eyasu Tigabu, Senior AMR/Lab Advisor Health Security Activity Project, ASM consultant paid a visit to Tibebe Ghion Specialized Hospital to evaluate the impact of their joint support.

During the visit, the delegation focused on the hospital’s bacteriology laboratory, which has been substantially strengthened through ongoing collaborative efforts. The tour allowed representatives to directly observe the practical results, upgraded capabilities, and operational improvements resulting from Project HOPE’s technical and resource support.

Following the laboratory assessment, the leadership team held strategic discussions with officials from the College of Medicine and Health Sciences. The meetings centered on evaluating current benchmarks and identifying opportunities to further strengthen and expand the strategic collaboration in the areas of mutual interest.

Follow us on:

Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu?mibextid=ZbWKwL
Website:
bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information_office_CMHS_BDU
Twitter:
twitter.com/medicine_bdu?t…
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/college-of-medicine-and-health-sciences-bahir-dar-university-ethiopia/
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbDGGfm8fewo1atUCH3p

14/09/2026

ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ (በድጋሜ የወጣ)
=====================
04/01/2019 ዓ.ም

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ የኮሌጁ የሕክምና ትምህርት እና አገልግሎት ምክትል ድሬክተር (Deputy Director, Medical Education and Services) ቦታ መመደብ ይፈልጋል፡፡

የማወዳደሪያ መሥፈርት
==============
1ኛ. የትምህርት ደረጃ ሁለተኛ ዲግሪ(ሌክቸረር) እና ከዚያ በላይ ማዕረግ ያለው/ያላት፣
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በጥናትና ምርምር ወይም መሰል ተቋማት፣ በመማር ማስተማር፣ ሕክምናና ማኅበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የሕክምና ትምህርትና አገልግሎት ተደራሽነት፣ ፍትሐዊነት፣ ጥራትንና ደኅንነት፣ ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ኮሌጁን የትምህርትና አገልግሎት የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እና ክሱትነቱን ለመጨመር፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ (ስልታዊ) ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣
4ኛ. ከኮሌጁ የሚሰጠውን ዝርዝር ኃላፊነት በቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት ተቀብሎ በከፍተኛ ብቃት የሚፈፅም፣
5ኛ. የኮሌጁ አመራሮች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የሕክምና ትምህርት መምሕራን ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፣
6ኛ. ከትምህርት ወይም ምርምር ወይም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መደበኛ የሥራ እረፍት ላይ ያልሆነ/ች እና ለቀጣይ ሦስት ዓመት በኃላፊነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች::

አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (04/01/2019 ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት አምስት (05) ተከታታይ ቀናት የሚከተሉትን ሰነዶች ማለትም
1. ማመልከቻ ደብዳቤ፣
2. ግለ ታሪክ('CV')፣
3. የትምህርትና የሥራ/አመራርነት ልምድ (በሰው ሀብት አስተዳድር ልማት ቢሮ የረጋገጠ) ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም
4. ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ
በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ድሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የመመዝገቢያ ቦታ
==========
ጥበበ ግዮን ካምፓስ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ባሕር ዳር

Address

Amhara Region
Bahir Dar
79

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when College of Medicine and Health Sciences, Bahir Dar University, Ethiopia. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to College of Medicine and Health Sciences, Bahir Dar University, Ethiopia.:

Shortcuts

Share