12/08/2026
🦴 የጀርባ ህመም፦ መቼ መጨነቅ አለብን?
የጀርባ ህመም በብዙዎቻችን ላይ የሚከሰትና በዕለት ተዕለት ኑሯችን ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር የተለመደ የጤና ችግር ነው። ነገር ግን ሁሉም የጀርባ ህመም ተመሳሳይ አይደለም፤ አብዛኛው በቀላል ምክንያቶች የሚከሰቱ ሲሆን፣ ሌሎቹ ግን ተገቢ የሕክምና ምርመራና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሊሆኑ ይችላሉ
🔹 1. ቀላል የጀርባ ህመም (Mild Back Pain)
• መነሻው ፦ ከከባድ ሥራ፣ ከተሳሳተ አቀማመጥእና አተኛኘት (Poor Posture) ወይም ከወገብ ጡንቻ ተደጋጋሚ ጉዳት ሊመጣ ይችላል።
• መፍትሄው ፦ አብዛኛውን ጊዜ በዕረፍት፣ በቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ትክክለኛ አቀማመጥን እና አተኛኘትን በማስተካከል በሂደት ይጠፋል
የጀርባ ህመም ከነርቭ ጫና ሊመጣ የችላል
🔹 2. ከጀርባ ወደ እግር የሚወርድ ህመም (Radiating Pain or Sciatica)
• ምልክቱ ፦ ህመሙ ከጀርባ ተነስተቶ ወደ እግር የሚወርድ ከሆነ፣ የመደንዘዝ ፡ የማቃጠል ወይም የመውጋት (in mbbess and Burning pain) ስሜት ካለው።
• ምክንያቱ ፦ ይህ ምልክት በነርቭ መተላለፊያ ቱቦ ውሰጥ ወይም የነርቭ መውጫ ቀዳዳ አካባቢ የነርቭ ጫና (Nerve Compression/Sciatica) መኖሩን ሊያሳይ ይችላል
🔴 3. አስጊ ምልክቶች — አፋጣኝ ምርመራ የሚሹ! (Red Flags! ⚠️)
የሚከተሉት ምልክቶች ካሉብዎ ሳይዘገዩ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የህክምና ተቋም መሄድ አለብዎት፦
1️⃣ ከባድ ወይም እየባሰ የሚሄድ ህመም
2️⃣ የእግር መዛል ወይም ድክመት
3️⃣ የሽንት ወይም የሰገራ መቆጣጠር ችግር
3️⃣ ከፊንጢጣ እስከ ብልት በለው የሰውነታችን አካባቢ መደንዘዝ
⚠️ እነዚህ ምልክቶች አስቸኳይ የሕክምና ምርመራና እርዳታ ይፈልጋሉ!
💡 ለጀርባ ጤንነት ምክሮች
የጀርባ ህመም እንዳይከሰት ወይም እንዳይባባስ እነዚህን ቀላል ልምዶች ያዘውትሩ፦
• 🏋️ ክብደት ሲያነሱ፦ በወገብዎ ከመታጠፍ ይልቅ ጉልበትዎን አጥፈው ይነሱ።
• 🪑 አቀማመጥዎን እና አተኛኘትቶን ያስተካክሉ፦ በቢሮም ሆነ በቤት ሲቀመጡ ጀርባዎን ቀጥ አድርገው ይቀመጡ።
• 🛏️ በጀርባ ሲተኙ አንገት ስር አነስተኛ ትራስ፡ ጉልበቶ ሥር ከፍ ያለ ትራስ እንዲሁም በጎኖ ሲተኙ ጉልበቶ መሀል ትራስ ያድርጉ። ይህ የአከርካሪ አጥንቶን የተፈጥሮ ቅርፅ ስለሚጠብቅ ጀርባዎ እረፈት አግኝቶ አንዲያድር ያደርጋል
• 🚶 አዘውትረው ይንቀሳቀሱ፦ ለረጅም ሰዓታት ተቀምጠው አይስሩ፤ በየሰዓቱ በመነሳት ትንሽ ዘና ይበሉ።
Michot home based clinic