Debre Markos city administration health office

Debre Markos city administration health office በዚህ ገፅ ዓለም አቀፋዊ፣ አገራዊ፣ ክልላዊ፣ የከተማውንና የአካባቢውን ወቅታዊ የጤና ጉዳይ መረጃዎችን እናጋራለን።

07/08/2026
የጡት ማጥባት አስፈላጊነት እና ጥቅሞች:_________የጡት ማጥባት ለሕፃናት ጤናማ እድገትና የበሽታ መከላከል አቅም እንዲሁም ለእናቲቱ ጤና እጅግ አስፈላጊ የሆነ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው። ህጻና...
05/08/2026

የጡት ማጥባት አስፈላጊነት እና ጥቅሞች:
_________

የጡት ማጥባት ለሕፃናት ጤናማ እድገትና የበሽታ መከላከል አቅም እንዲሁም ለእናቲቱ ጤና እጅግ አስፈላጊ የሆነ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው። ህጻናት በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት የእናት ጡት ወተት ብቻ (EBF) ማግኘት አለባቸው።

👉በጡት ማጥባት ወቅት ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ፦

▪️የመጀመሪያውን ወተት (እንገር / Colostrum) ለህጻኑ ይስጡ:- እንገር የመጀመሪያው የእናት ወተት ሲሆን ሕፃኑን ከበሽታዎች የሚጠብቅ በጣም ከፍተኛ የመከላከያ ኃይል ያለው ነው። ይህ ወተት ከፍተኛ የበሽታ መከላከል አቅም ያላቸውን ንጥረ ነገሮች ይዟል።

▪️ጡት ማጥባትን በመጀመሪያው 1 ሰዓት ውስጥ ይጀምሩ:- ሕፃኑ ከተወለደ በኋላ በመጀመሪያው 1 ሰዓት ውስጥ ጡት ማጥባት መጀመር ለሕፃኑ ሕይወት ማዳን፣ ለእናቱም ፈጣን ማገገም ይረዳል። እንዲሁም የጡት ወተት ምርት በቶሎ እንዲጀምር እና በቂ የሆነ ወተት እንዲመነጭ ያደርጋል።

▪️ህጻኑ/ኗ በፈለገ/ች ጊዜ ያጥኑ:- ሕፃኑ/ኗ በፈለገ/ች ጊዜ በቀንና በሌሊት በተደጋጋሚ ጡት ያጥቡ። ይህ የወተት ምርትን ያበረታታል።

▪️ትክክለኛ የማጥባት ሁኔታን ይጠቀሙ (Positioning & Latching)፦ በአግባቡ ለማጥባት እናቲቱ በተመች ሁኔታ ተቀማጣ ማጥባት አለባት። ሕፃኑ አፉን በደንብ ከፍቶ ጠቆር ያለዉን የጡትዎን ክፍል አብዛኛዉን በመጉረስ፣ ጉንጮቹ ሞላ በመድረግና በመሀል ትንሽ እያረፈ በደንብ መሳቡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

▪️ሙሉ በሙሉ በጡት ወተት ብቻ ማሳደግ፦ በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ውስጥ ውሃን ጨምሮ ምንም አይነት ተጨማሪ ምግብ ወይም ፈሳሽ ሳይሰጥ በጡት ወተት ብቻ ህጻናትን ማሳደግ ይገባል። ይህም የጡት ወተት በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ለህጻናት እድገት የሚያስፈልጉትን ንጥረ ምግቦች እንዲሁም ውሃን ስለሚይዝ ነው።

▪️የበሽታ መከላከል ጥቅሞች፦ የጡት ወተት ሕፃናትን ከተቅማጥ፣ ከሳንባ ነቀርሳ (Pneumonia) እና ከጆሮ ኢንፌክሽን የሚከላከል ሲሆን እናቶችንም ከጡት እና ከማህፀን ካንሰር ተጋላጭነት ይከላከላል።

▪️በህመም ወቅት ጨምረው ጡት ያጥቡ:- ከ 6 ወር በታች የሆኑ ህጻናት በተለያየ ህመም በሚጠቁበት ወቅት ከሌላ ጊዜ አብልጠው/ጨምረው ያጥቡ። ይህም በህመም ወቅት በሽታን ለመቋቋም እንዲሁም በቶሎ ለማገገም ይረዳቸዋል።

▪️ከ6 ወር ጀምሮ(181 ቀን) ከተጨማሪ ምግብ ጎን ለጎን ጡት ማጥባትን ይቀጥሉ:- ከ 181ኛ ቀን ጀምሮ እድሜውን የሚመጥን፣ የተመጣጠነና የተሰባጠረ ተጨማሪ ምግብ በመጀመር ጡት ማጥባቱን እስከ 2 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ይቀጥሉ።

▪️የበቂነት ምልክቶች፦ ሕፃኑ በቀን ቢያንስ ከ6-8 ጊዜ የሚሸና ከሆነ እና በቂ የክብደት እድገት የሚያሳይ ከሆነ፥ ህጻኑ በቂ ወተት ማግኘቱን ማረጋገጥ ይቻላል።

▪️የእናቶች ስነ-ምግብ ሁኔታ፦ የሚያጠቡ እናቶች ከሌላው ጊዜ ተጨማሪ ሁለት ጊዜ የተሰባጠረ ምግብ ማገኘት የሚገባዘው ሲሆን፣ በቂ ፈሳሽ (ውሃ፣ ሾርባ) እና አትክልትና ፍራፍሬዎችንም አብዝተው መመገብ ይኖርባቸዋል።

👉 የአባቶች እና የቤተሰብ ሚና፦

▪️የቤት ውስጥ ስራዎችን ማገዝ፦ አባቶችና ቤተሰብ የሚያጠቡ እናቶችን በቤት ውስጥ ስራ በማገዝ በቂ የእረፍት ጊዜ እንዲኖራቸው ማድረግ አለባቸው።

▪️ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ መስጠት፦ በእናቶች ላይ የሚፈጠረውን ድካም እና ጭንቀት ለመቀነስ አዎንታዊ እና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ ማድረግ ወሳኝ ነው።

▪️የተመጣጠነ ምግብ ማቅረብ፦ እናቲቱ በቂ እና የተመጣጠነ ምግብ ማግኘቷን ማረጋገጥ እና ማበረታታት።

የመረጃ ምንጭ: Ministry of Health,Ethiopia

04/08/2026
01/08/2026

የአማራ ክልል የ2019 ዓመታዊ በጀት ከ402 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ኾኖ ጸደቀ።

የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤ በ2019 በጀት ዓመት ለክልሉ የልማት ሥራዎች ማስፈጸሚያ በጀት 402 ቢሊዮን 285 ሚሊዮን 713 ሺህ 544 ብር ኾኖ አጽድቋል።

የ2019 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀቱ በ2018 በጀት ዓመት ከተመደበው የ78 ነጥብ 4 በመቶ ወይም የ176 ቢሊዮን 831ሚሊዮን 934 ሺህ 307 ብር ዕድገት እንዳለው የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኀላፊ አታላይ ጥላሁን ገልጸዋል፡፡

ከዓመታዊ በጀቱ 71 ነጥብ 3 በመቶ የሚኾነው በክልሉ ከሚሠበሠብ ገቢ፣ 27 ነጥብ 6 በመቶ የሚኾነው ከፌዴራል መንግሥት ጥቅል የቀመር መደበኛ ድጋፍ ድርሻ እንዲኹም ቀሪው ደግሞ ከልዩ ልዩ ምንጮች እንደሚሸፈን ተገልጿል።

የተመደበው በጀት በዓመቱ ለዘላቂ ልማት ዕቅድ ማስፈጸሚያ፣ ለልዩ ልዩ ሪፎርሞች እና መዋቅራዊ ማሻሻያዎች፣ ለድህነት ተኮር ሥራዎች እና የክልሉን የመልማት አቅም ታሳቢ ያደረገ ስለመኾኑም ተመላክቷል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት የክልሉ መንግሥት ሥራ ላይ ላዋለው ከ39 ነጥብ 1ቢሊዮን ብር በላይ የተጨማሪ በጀት አጽድቋል።

ለአመታት በጎዳና ላይ የነበሩ እናት እና ልጅ ወደ ማዘር ትሬዛ በጎ አድራጎት ድርጂት ተወሰዱ።=======================ሃምሌ 24, 2018ዓ.ም: ለአመታት ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ይ...
31/07/2026

ለአመታት በጎዳና ላይ የነበሩ እናት እና ልጅ ወደ ማዘር ትሬዛ በጎ አድራጎት ድርጂት ተወሰዱ።
=======================

ሃምሌ 24, 2018ዓ.ም: ለአመታት ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ይኖሩ የነበሩ አናት እና ልጅ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጭዎች አማካኝነት ወደ ማዘር ትሬዛ በጎ አድራጎት ድርጂት ተወስደዋል።

እናት እና ልጅ ሁለቱም ውስብስብ የጤና ችግሮች (በተለይ ልጂት አይነስውር፣ የአእምሮ ችግር፣ መቆም እና መንቀሳቀስ አለመቻል....) ያለባቸው በመሆኑ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጭዎች አማካኝነት ወደ ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ተወስደው የምርመራ እና ህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል። በኋላም በተለያዮ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እና ትብብር ወደ ማዘር ትሬዛ በጎ አድራጎት ድርጂት በቋሚነት እንዲኖሩ ተመቻችቶ ተወስደዋል።

ይህን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሰጡ የህዳሴ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች፣ ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ አፖረንት የወጡ ተማሪዎች፣ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ እና ሴቶች ጉዳይ መምሪያ ሰራተኞች ሲሆኑ እናት እና ልጅ በቀጣይ ተከታታይ ምርመራ እና ህክምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል።

እኒህ እናት እና ልጅ በህብረተሰቡ ማህበራዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው ለብዙ አመታት በጎዳና ላይ ይኖሩ እንደነበር ይታወቃል ፤ በሌላ በኩል ማዘር ትሬዛ በጎ አድራጎት ድርጂት ለረጅም አመታት አካላዊና አእምሯዊ የጤና ችግር ያለባቸውን ልጆች በቋሚነት ይዞ እየረዳ ያለ እና ሌሎች ማህበራዊ ድጋፎችን የሚሰጥ በጎ አድራጎት ድርጂት ነው።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እናመሠግናለን!-----------------------------------------በ2018 በጀት አመት በከተማችን ለሚኖሩ ለ100 ዝቅተኛ ኗሪዎች የጤና መድህን የአባልነት ክ...
31/07/2026

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እናመሠግናለን!
-----------------------------------------

በ2018 በጀት አመት በከተማችን ለሚኖሩ ለ100 ዝቅተኛ ኗሪዎች የጤና መድህን የአባልነት ክፍያ በመክፈል የጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርገዋል።

30/07/2026

በኢትዮጵያ የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ እና የኮንዶም ዕጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ::

በአገሪቱ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኙ ሰዎች ቁጥር 700 ሺህ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 24 የሆኑ ወጣት ሴቶች እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለከፍተኛ ተጋላጭነት መዳረጋቸው ተጠቁሟል።

የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕ ፕላስ) በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ አሁን ላይ በአገሪቱ ከፍተኛ የኮንዶም ዕጥረት የተከሰተ ሲሆን የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭትም በስጋት ደረጃ እየጨመረ ይገኛል።

1. በአገሪቱ ከግማሽ ሚሊየን በላይ፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ እስከ 700 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ይገኛል።

2. ቫይረሱ በደማቸው ከሚገኙ ሰዎች መካከል 36 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። በተለይም ከ14-24 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣት ሴቶች እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለስርጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ ናቸው።

3. በአገሪቱ ያለው ከፍተኛ የኮንዶም ዕጥረት ለስርጭቱ መጨመር ተጨማሪ ስጋት ደቅኗል።

ምስረታው 22 ዓመታትን ለማስቆጠር የተቃረበውና ከ500 በላይ ማህበራትን በስሩ ያቀፈው ኔፕ ፕላስ፣ በሚቀጥለው ወር 21ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ታደሰ አስታውቀዋል።

ይህ ጉባዔ በአሁኑ ወቅት ትኩረት በማጣቱ እየተዘነጋ የመጣውን፣ ነገር ግን አሁንም የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ የሚገኘውን የኤችአይቪ ህመም አስመልክቶ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች የሚሰሩበት ይሆናል።

በተጨማሪም ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ያካሄደውን "Stigma index research" ጥናት ተከትሎ፣ አሁን ላይ ሶስተኛውን ዙር ጥናት እያካሄደ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በሚቀጥለው ወር በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከኔፕ ፕላስ አባል ማህበራት የተወከሉ 120 ያህል እንግዶች ይሳተፋሉ።

Via Ethio FM
ዘገባ፦ እስከዳር ግርማ
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም

30/07/2026

Address

Ethiopia, Amhara Region
Debra Markos

Telephone

+251587711940

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Markos city administration health office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Debre Markos city administration health office:

Shortcuts

Share