W/ro Siheen General Hospital

W/ro Siheen General Hospital ዘመኑን በዋጀ ዘመናዊ የህክምና መሳርያወች በመታገዝ ከፈተኛ የሰራ ልምድ ባላችው ሐኪሞች ጥራቱን የጠበቀ ህክምና ከመልካም መሰተንግዶ ጋር እኛጋ ያገኛሉ�

አስከሬን አይሰጥም 🙄በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም ተባለህይወታቸው ካለፈ በኋላ አስከሬኑ የማይታጠብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ...
21/11/2025

አስከሬን አይሰጥም 🙄

በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም ተባለ

ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አስከሬኑ የማይታጠብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የቀብር ስርዓታቸው ይፈፀማል ተብሏል።

ቀብር የተፈፀመባቸው ቦታዎችም በደንብ መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልጿል።

ማህበረሰቡ የበሽታውን ከባድነት ተረድቶ ይህንን ውሳኔ መቀበል እና መተባበር አለበት ተብሏል።

በሌላ በኩል ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ለአንድ አመት ጊዜ የሚቆይ በመሆኑ፥ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ አለባቸው ነው የተባለው።

ተገቢው ክትትል እና ህክምና ተደርጎለት የዳነ ሰው በሽታውን ማስተላለፍ አይችልም።

እንደ ኮሮና ቫይረስ በአየር ይተላለፋል የሚል የተዛባ አመለካከት መኖሩ የተገለፀ ሲሆን፥ ህመሙ በአየር የማይተላለፍ ነው ተብሏል።

ህመሙ በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ ህመሙ ካለባቸው ሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ከንክኪ የራቀ መሆን እንዳለበትም ተገልጿል።

ማርበርግ እንደ ኮቪድ በአየር የሚተላለፍ ባይሆንም፥ ከኮቪድ በበለጠ ህይወት የሚነጥቅ ነው።

እንደ ወረርሽኙ ክብደት የሞት ምጣኔው ከ24 እስከ 88 በመቶ ይደርሳል።

33 ሰዎች ተመርምረው 6 ሰዎች ህመሙ የተገኘባቸው ሲሆን፥ ሶስቱ ህይወታቸው ሲያልፍ ሶስት ሰዎች ደግሞ በህይወት አሉ ተብሏል።
==========≠============
💎👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ጤና ነክ የሆኑ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
- ፌስቡክ: https://www.facebook.com/profile.php?id=61559230067564&mibextid=ZbWKwL
- ቴሌግራም:https://t.me/woizero_siheen_general_hospital

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when W/ro Siheen General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category