07/05/2022
የጥርስ መቦርቦር (Dental Caries)
ጥርስ ተቦረቦረ የሚባለዉ በጥርስ ላይ በሚቀሩ የምግብ ትርፍራፊዎች ላይ በሚኖረዉ ባክቴሪያ(S.mutans) አማካኝነት ጥርሳችን ተፈጥሯዊ መልኩን ሲቀይርና ሲሸራረፍ ነው፡፡
ለጥርስ መቦርቦር አጋላጭ ነገሮች
✍️ ምግብን ከተመገቡ በኋላ አፍ
የማፅዳት ባህል አለመኖር
✍️ ጣፋጭነት ያላቸዉን ምግቦች አዘውትሮ አለ
መመገብ።
✍️ ሲጋራና ትባሆ ማጨስ
በእርግዝና ወቅት የእናት ለሊድ ተጋለጭ
መሆን
👉 ምልክቶቹ
🔹 ነጭ የነበረው የጥርስ አካል ወደቡናማ
ቀለም መቀየር
🔹 መጥፎ የአፍ ጠረን
🔹 ጣፋጭ ነገሮችና ሞቃት ወይም
ቀዝቃዛ ምግብና መጠጦችን
ስንጠቀም የህመም ስሜት መኖር
🔹 በአይን የሚታይ የበለዘ፣ የተቦረቦረና
የተሸረፈ ጥርስ መኖር
👉 ጥርስ መቦርቦር ህክምና
ጥርስን መሙላት(Filling)
ጥርስን መተካት(Dental restoration)
ጥርስን መንቀል(extraction)
👉 መከላከያ ዘዴዎች
🔹 ከምግብ በኋላ አፍን በውሀ ማፅዳት
🔹 ስኳር የበዛበት ምግብን አለማዘወተር
🔹 ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ፍሎራይድ
ያለበትን የጥርስ ሳሙና መቦረሽ።
ለተጨመሪ መረጃ ሼር ያድርጉ
👇👇👇👇👇
ድሬ መካከለኛ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ
ድሬዳዋ:- ጋራድ ህንጻ 2ኛ ፎቅ