Dr.Solomon, MFM ዶ/ር ሰለሞን ልዮ የነፍሰጡር እናቶች ህክምና

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • Dr.Solomon, MFM ዶ/ር ሰለሞን ልዮ የነፍሰጡር እናቶች ህክምና

Dr.Solomon, MFM ዶ/ር ሰለሞን ልዮ የነፍሰጡር እናቶች ህክምና ሰኞ, እሮብ,ቅዳሜ - በ ሀበሻ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊቲ ክሊኒ?

እንኳን ደስ ያላችሁ!!!   Congratulations! በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማህጸንና ጽንስ ትምህርት ክፍል ላለፉት አራት አመታት...
01/01/2023

እንኳን ደስ ያላችሁ!!! Congratulations!

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማህጸንና ጽንስ ትምህርት ክፍል ላለፉት አራት አመታት በጽንስና ማህጸን ህክምና ስፔሻሊቲ (Specialty in Gynecology and Obstetrics) ትምህርት ያሰለጠናቸውን ሀኪሞች አስመርቀናል።

መላው አስተማሪዎቻችሁ እና የት/ት ክፍሉ የተሰማንን ከፍተኛ ደስታ እየገለፅን ቀጣዩ የስራ ዘመናችሁ በስኬት የተሞላ እንዲሆን እንመኛለን።

እንኳን ደስ ያላችሁ!!!

Congratulations!

በፐሬድ ወቅት የሚፈሰው የደም መጠን መብዛትፐሬድ የሚበዛባቸው ምክንያቶች ምንድናቸው?  ይሄ እንደ ሰዉ ሁኔታና ከሰው ሰውም ምክኒያቱ ይለያያል።አብዛኛውን ጊዜ ምንም ምክኒያት ሳይኖር የወር አ...
08/06/2022

በፐሬድ ወቅት የሚፈሰው የደም መጠን መብዛት

ፐሬድ የሚበዛባቸው ምክንያቶች ምንድናቸው?

ይሄ እንደ ሰዉ ሁኔታና ከሰው ሰውም ምክኒያቱ ይለያያል።አብዛኛውን ጊዜ ምንም ምክኒያት ሳይኖር የወር አበባ ሊበዛ ይችላል።

የፐሬድ መብዛት የሚያስከትሉ ሁኔታዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ።

● ከኦቫሪዎቹ አንዱ ለአንድ ወር ወይም ከዚያም በላይ እንቁላል ማዘጋጀት ካቆመ

● የማህጸን እጢ

● በደም መርጋት ችግር

● አንዳንድ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ወይም ደም ለማቅጠን የሚወሰዱ መድሃኒቶች የጎን ተፅዕኖዎች

● ከየታይሮይድ ዕጢ ጋር (ሆርሞኖችን የሚያመነጭ ዕጢ) ጋር የተያያዙ ችግሮች

● የማሕጸን ካንሰር

በፐሬድ ወቅት የሚፈስ የደም መጠን የተለመደው ምን ያህል ነው?

የተለመደው የፐሬድ ጊዜ ከ 8 ቀናት ያነሰ ነው። ከስር የተዘረዘሩት ፐሬድ የበዛ መሆኑ የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው

● ሙሉ በሙሉ እየራሰ በ1 ወይም 2 ሰአት ውስጥ አንድ ሞዴስ የቀየሩ እንደሆነ

● ከፍተኛ መጠን ያለው ደም (የረጋ ደም) የፈሰሰ እንደሆነ

የፐሬድ የደም መፍሰስ ድንገተኛ ወይም አደገኛ የሚሆነው ምን ሲሆን ነው?

የፐሬድ የደም መፍሰስ አደገኛ ሊሆን የሚችለው

1. በ 2 ሰዓታት ውስጥ 4 ወይም ከዚያ በላይ ሙሉ በሙሉ የራሰ ሞዴስ ከቀየሩ ሃኪምዎን ያማክሩ ወይም ወደ ድንገተኛ ክፍል ይሂዱ።

2. ነፍሰ ጡር ከሆኑና ደም ከፈሰሰም ድንገተኛ ነው

በፐሬድ ወቅት ዶክተር ወይም ነርስ ማየት ያለብኝ ምን ስሆን ነው?

● ነፍሰጡር ነኝ ወይም ልሆን እችላለሁ ብለው ካሰቡ

●ፐሬድዎ ከ 8 ቀናት በላይ የሚቆይ ከሆነ

● ሙሉ በሙሉ እየራሰ በ1 ወይም 2 ሰአት ውስጥ አንድ ሞዴስ የቀየሩ እንደሆነ

● ብዙ ደም እየፈሰሰዎት ስለሆነ ሁለት ሞዴሶች ደራርበው መጠቀም ካስፈለግዎት

● ለሊት ተነስተው ሞዴስ መቀየር ካስፈለግዎት

● ከ 1 ኢንች የበለጠ የረጋ ደም የፈሰሰ እንደሆነ

● ፐሬድ ከጨረሱ በኋላ በድጋሚ ያለጊዜው ፐሬድ ካዩ

● በፐሬድወቅት የሆድ ህመም ካለ

● መጸነስ እየፈለጉ ካልቻሉ

● ቢያንስ ለአንድ አመት ፐሬድ ሳያዩ ከቆዩ በኋላ ደም ከፈሰሰ ፤ ማለትም ካረጡ በኋላ ደም ካዩ

● ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ከታዩ እና የደም ማነስ ካስከተለብዎት

የደም ማነስ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው
አቅም ማነስ
ከፍተኛ የድካም ስሜት
ራስ ምታት
በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጊዜ የመተንፈስ ችግር
የልብ ምት መጨመር

ላደርጋቸው የሚገባኝ ምርመራዎች አሉን?

የሚያስፈልጉት ምርመራዎች በእድሜ ፣በህመሙ ሁኔታ እና በግለሰብ ሁኔታዎች ይወሰናል። ምርመራዎቹ የሚከተሉት ሊያካትቱ ይችላሉ።

● የደም ምርመራዎች

● ከማህፀን ናሙና ተወስዶ ምርመራ

● አልትራሳውንድ

● ሂስተሮስኮፒ

የፐሬድ መብዛት ህክምናው ምንድን ነው?

ህክምናው እንደ መንስኤው ይለያያል። አብዛኛውን ጊዜ ሕክምና ላያስፈልግ ይችላል።ካስፈለገ ግን ህክምናዎቹ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ።

● ሆርሞኖች ያላቸው የወሊድ ቁጥጥር ዘዴዎች

● የደም መቅጠን የሚቀንሱ መድሃኒቶች

●እብጠት የሚቀንሱ መድሃኒቶች

● ፕሮጄስቲን የተባለ ሆርሞን ያላቸው መድሃኒቶች

● ኦቫሪዎችን ለአጭር ጊዜ ሥራቸውን እንዲያቆሙ
የሚያደርጉ መድሃኒቶች

● በቀዶ-ጥገና የማህጸን እጢ ወይም ሌሎች እባጮችን ማስወገድ

በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ጠቃሚ ጽሁፎች ለማንበብ ገፃችን "ላይክ" ያድርጉ::

ስልምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች መረጃ ለማግኘት በ 0961999109 ይደውሉ::
ሐበሻ የጽንስና የማህጸን ልዩ ክሊኒክ
አድራሻ:- ጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ፊት ለፊት ላመርገየር ሆቴል ጀርባ
ስልክ ቁጥር 0961999109/0582116658
ጎንደር ኢትዮጵያ

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ማቅለሽለሽና ትውከት በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ማቅለሽለሽና ትውከት ምንድን ነው? ይህ ብዙውን ጊዜ ከእርግዝና ጋር የሚከሰት ሲሆን ጠዋት ጠዋት ብቻ፣ ቀትር ላይ ፣ ከ...
08/06/2022

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ማቅለሽለሽና ትውከት

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ማቅለሽለሽና ትውከት ምንድን ነው?

ይህ ብዙውን ጊዜ ከእርግዝና ጋር የሚከሰት ሲሆን ጠዋት ጠዋት ብቻ፣ ቀትር ላይ ፣ ከሰአት በኋላ ወይም ቀኑን ሙሉ ያለማቋረጥ ሊከሰት የሚችል ነገር ነው።በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ማቅለሽለሽና ትውከት አብዛኛውን ጊዜ በመጀመሪያዎቹ 3-4 የእርግዝና ወራት ውስጥ እየቀነሰ ሄዶ ይቆማል።

በእርግዝና ጊዜ የሚከስት የማቅለሽለሽና ትውከት ስሜት እንዲቀንስልኝ ምን ማድረግ አለብኝ?

የሚከተሉት በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ማቅለሽለሽና ትውከት እንዲቀንስ ይረዳሉ

● ቅባት የበዛባቸውና ቶሎ የማይፈጬ ምግቦችን አለመመገብ

● በቀን ውስጥ አነስ አነስ ያሉ ምግቦችን ቶሎ ቶሎ መመገብ

● ጥዋት ሲነሱ ከመኝታ ሳይወርዱ ደረቅ ዳቦ መብላት

● ሎሚ መምጠጥ

● ቀጭን የቅርንፉድ ሻይ በቀን 3 ጊዜ መጠጣት

● በሃኪም የሚታዘዙ የትውከት መድሃኒቶችን መውሰድ

ሃኪም ማየት ያስፈልገኛል?

ከማቅለሽለሹ ጋራ አብሮ ማስታወክ ካለ፣ በዚህም ምክኒያት ምግብ የማይረጋ ከሆነና የክብደት መቀነስ ካስከተለ ሃኪም ቤት ሄዶ ህክምና ማድረግ ያስፈልጋል።

በተጨማሪም ከስር የተጠቀሱት ምልክቶች ከታዩ ሃኪም ማማከር አስፈላጊ ነው

● ደም የቀላቀለ ትውከት

● ከባድ የሆድ ቁርጠት ወይም ህመም

● የሰውነት የፈሳሽ መጠን መቀነስ ምልክቶች ለምሳሌ የሽንት መጠን መቀነስ ፣ የሽንት መቅላት ፣ ከተቀመጡበት ሲነሱ መንገዳገድ

እንዲህ በሚሆንበት ጊዜ በደም ስር የሚሰጥ ፈሳሽ እና የትውከት ማስታገሻ መድኃኒት መውሰድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ።

በማህፀንና ፅንስ ህክምና ዙሪያ ጠቃሚ ጽሑፎችን ለማንበብ ገጻችንን ይከታተሉ( like ያድርጉ)

ነፃ የመሴንጀር የምክር አገልግሎት ተጠቃሚ ይሁኑ

ስለ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች መረጃ ለማግኘት በ0961999109 ይደውሉ
ሐበሻ የጽንስና የማህጸን ልዩ ክሊኒክ
አድራሻ:- ጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ፊት ለፊት ላመርገየር ሆቴል ጀርባ
ስልክ ቁጥር 0961999109/0582116658
ጎንደር ኢትዮጵያ

Habesha Obstetrics & Gynecology Clinic wish Happy Mother's Day to all moms out there!
08/05/2022

Habesha Obstetrics & Gynecology Clinic wish Happy Mother's Day to all moms out there!

07/05/2022
02/05/2022

Eid Mubarak to all muslim brothers and sisters from Habesha maternity clinic

24/04/2022

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዬች እንኳን ለ ብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

20/03/2022

በቅድመ ወሊድ ጀምሮ የሚከሰትየፅንሱ የኩላሊት ሽንት መቋጠር ( Fetal Hydronephrosis) ምንድነው?

መግቢያ

በአሁኑ ጊዜ በእርግዝና ወቅት የአልትራሳውንድ ምርመራ መጨመር የfetal hydronephrosis (ANH) እውቅና እንዲጨምር ማድረጉ ይታወቃል። Hydronephrosis ማለት ከተለመደው በላይ ኩላሊት ውሃ የመቋጠር ችግር ማለት ነው። ANH ማለት ደግሞ በእርግዝና ወቅት የጽንሱ ላይ Hydronephrosis ሲኖር የሚሰጥ ስያሜ ነው።

በአልትራሳውንድ ምርመራ ጊዜ መመዘኛዎቹን በማሟላት hydronephrosis (ANH) የመገኘት እድሉ በቅድመ ወሊድ ከሚታዩ አጠቃላይ እናቶች ውስጥ ከ0.6 እስከ 6% ይደርሳል።

ከነዚህ ውስጥ 20-50% በሁለቱ ኩላሊቶች ሲከሰት፣ አልፎ አልፎ ደግሞ ከሌሎች ተጨማሪ እክሎች ጋር ይያያዛል።

ይህ የኩላሊት ውሀ የመቋጠር ችግር (ANH) አጠቃላይ ውጤቱ በሚያስከትለው ምክንያት (Etiology) ይወሰናል። (ስለምክንያቶቹ ቀጣይ ክፍል ላይ እናያለን!) ።

ምንም እንኳን ከ40-85% የሚሆነው ANH በወሊድ ወይም በጨቅላነት ጊዜ ቢጠፋም ፣ከ15-20% የሚሆኑት ህክምና (ቀዶ ህክምና) የሚያስፈልጋቸው ያልተለመዱ ምክንያቶች ይኖራሉ። ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ሽንት ከሽንት ፊኛ ወደ ኩላሊት መመለስ (VUR) እና የሽንት ቱቦዎች ኢንፌክሽኖች (UTI) በበርካታ እጥፍ ከፍ ያለ ይሆናል።

ስለሆነም የረዥም ጊዜ ክትትል ወይም የቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸው ከባድ ሕመም ያለባቸውን ሕፃናት ከጊዜያዊ hydronephrosis ካለባቸው እና አነስተኛ ምርመራዎች ከሚያስፈልጋቸው መለየት አስፈላጊ ነው።

ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: Pediatric Surgeon

በእርግዝና ጊዜ የሚመከር ጤናማ አመጋገብጤናማ አመጋገብ አስፈላጊ ከሚባሉት የጤናማ  የሂወት መርሆዎች መካከል ይጠቀሳል። በይበልጥ ደግሞ ለነፈሰጡር እናቶች እና ለመፀነስ በዝግጅት ላይ ላሉ እ...
19/03/2022

በእርግዝና ጊዜ የሚመከር ጤናማ አመጋገብ

ጤናማ አመጋገብ አስፈላጊ ከሚባሉት የጤናማ የሂወት መርሆዎች መካከል ይጠቀሳል። በይበልጥ ደግሞ ለነፈሰጡር እናቶች እና ለመፀነስ በዝግጅት ላይ ላሉ እህቶች እጅግ ጠቃሚ ነው።
ጤናማ አመጋገብ ለነፍሰጡር እናትና ለፅንሱ አስፈላጊ የሚባሉትን ቫይታሚኖችና ንጥረ ነገሮችን ይሰጣል።

የሚመከሩት የምግብ አይነቶች በ 5 ከፍለን እናያቸዋለን
1.አትክልቶች
2. ዳቦ እና የጥሪጥሬ ውጤቶች
3. ወተት፣ እርጎ፣ አይብ
4. ስጋ፣ አሳ
5.ፍራፍሬዎች

አታክልትና ፍራፍሬዎች

በተቻለ መጠን እንዲወሰዱ ከሚመከሩ ምግቦች ውስጥ የሚመደቡ ሲሆን ጠቃሚ ቫይታሚኖችንና ንጥረ ነገሮችን ይሰጡናል።
አታክልቶችን ስንጠቀም ንጥረ ነገሮቹን እንዳናጣ እና ለጥንቃቄ ሲባል በስሱ አብስለን ወይም በደንብ በውሀ አጥበን ቢሆን ይመከራል። አትክልትና ፍራፍሬዎችን ከመጠቀማችን በፊት በደንብ ማጠብ ይኖርብናል፣ በዚህም ሊኖሩ የሚችሉትን እንደ ቶክሶፕላዝሞሲስ የመሳሰሉትን ተህዋስያን ለማፅዳት ይጠቅማል።

ካርቦሀይድሬት (Starchy foods)

ካሎሪ ሳያበዙ ጠቃሚ ቫይታሚኖችንና ፋይበር ይሰጣሉ።
ከነዚህም ውስጥ የተለያዩ ዳቦዎች፣ ድንች፣ ስኳር ድንች፣ የበቆሎ ውጤቶች እና የ ገብስ ውጤቶች ይጠቀሳሉ።
እነዚህን ምርቶች ስንጠቀም በፋብሪካ ከተቀነባበሩት ይልቅ የተፈጥሮ ይዘታቸውን የጠበቁትን ምርቶች መጠቀም ይመከራል።

ፕሮቲን

ለፅንሱ እድገት እጅግ ጠቃሚ ሲሆኑ በየቀኑ የተወሰነ መጠን እንዲወስዱ ይመከራል። የፕሮቲን ምንጭ ከሚባሉት ውስጥ ስጋ፣ አሳ፣እንቁላል፣ ባቄላ እና ኦቾሎኒ ይጠቀሳሉ።

የወተት ተዋፅኦዎች

እንደ ወተት፣እርጎ እና አይብ የመሳሰሉትን የወተት ተዋፅኦዎች መጠቀም ለእናቲቱ እና ለ ፅንሱ እንደ ካልሲየም የመሳሰሉትን ንጥረ ነገሮች ለማግኘት ይረዱናል።

ተዘውትረው መወሰድ የሌለባቸው ምግቦች የትኞቹ ናቸው?

ጣፋጭ የሆኑ ምግቦች ማለትም እንደ ብስኩት፣ ኬክ፣አይስ ክሬም፣ ቸኮሌት እና ለስላሳ መጠጦች አይመከሩም። በተቻለ መጠን ጨው መጠቀምን መቀነስ ይመከራል።ፋትን ከ ኦቾሎኒ ቅቤ፣ ከ ዘይት ምርቶች እና ከአቮካዶ በመጠኑ መጠቀም ይመከራል።

በቂ ፈሳሽ መውሰድ ይመከራል

በእርግዝና ጊዜ በቂ ፈሳሽ መውሰድ መጠነ ሰፊ ጥቅም ያለው ሲሆን ጥቂት ለመጥቀስ ያህል፤ ለአጠቃላይ ጤንነት፣ ለእንሽርት ውሃ አስተዋፅኦ፣ ድርቀትን ለመከላከል እና ኪንታሮትን ለመከላከል ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።
በቀን ከ 8-10 ብርጭቆ ፈሳሽ መጠጣት ለጤናማ እርግዝና የሚመከር ሲሆን ለዚህም ነፁህ ውሃ፣ ፍሬሽ ጁስ፣ ሾርባ፣ ወተት ወዘተ መዉሰድ ይቻላል።ንፁህ የቧንቧ ውሀ መውሰድ የሚመከር ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በወስጡ ያለው ፍሎራይድ የተባለው ንጥረ ነገር ለህፃኑ ጥርስ እድገት በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ነው። የምንጠጣው ውሃ ይህን ንጥረ ነገር መያዙን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

ያሰታውሱ
ማንኛውንም አይነት የ አልኮል መጠጥ በማንኛውም መጠንና በማንኛውም የእረግዝና ጊዜ መጠቀም የተከለከለ ነው።
ለጠጨማሪ መረጃ በ0961999109 የደውሉ።
ሀበሻ የማህፀንና ፅንስ ህክምና
አድራሻችን: ጎንደር ላመርገየር ሆቴል በስተጀርባ

የወር አበባ (የፐሬድ) ህመምበፐሬድ ጊዜ ለምንድነው ህመም የሚኖረኝ?  በዚህ ወቅት ሰውነትዎ ፕሮስታግላንዲን የሚባሉ ኬሚካሎችን ያመነጫል።እነዚህ ኬሚካሎች በምጥ ጊዜ የሚኖረው አይነት የማህጸ...
19/03/2022

የወር አበባ (የፐሬድ) ህመም

በፐሬድ ጊዜ ለምንድነው ህመም የሚኖረኝ?

በዚህ ወቅት ሰውነትዎ ፕሮስታግላንዲን የሚባሉ ኬሚካሎችን ያመነጫል።እነዚህ ኬሚካሎች በምጥ ጊዜ የሚኖረው አይነት የማህጸን ቁርጠት ያመጣሉ። ይህ በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ህመም የጤና ባለሞያዎች ዲስመኖርያ( dysmenorrhea) በማለት ይጠሩታል።

አንዳንድ የማህጸን በሽታዎች በወር አበባ ወቅት የሚኖረውን ህመም ያባብሱታል። ይህ ችግር ከሚያባብሱት መካከል ኢንዶመትርዮሲስ፣ የማህጸን ኢጢ እና የማህጸን ኢንፌክሽን ተጠቃሽ ናቸዉ።

የህመም ስሜቱ ምን የመስላል?

የፐሬድ ህመም ያላቸው ሴቶች የታችኛው የሆድ አከባቢ ቁርጠት ይኖራቸዋል። ቁርጠቱ ቀላል ወይም ከባድ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም የጀርባ ወይም በጭን አከባቢ ህመም ሊኖር ይችላል። ህመሙ ፐሬድ እንደጀመረ ወይም ከመጀመሩ ከጥቂት ሰአታት በፊት ሊጀምር ይችላል።

አንዳንድ ሴቶች በተጨማሪ የሚከተሉት የህመም ስሜቶች ይታዬባቸዋል

● ማጥወልወል

● ተቅማጥ

● በጣም ከባድ የድካም ሰሜት

● ራስ ምታት

● ሆድ የመንፋት ስሜት

ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ ማድረግ የምችለው ነገር አለ?

አዎ የሚከተሉት በማድረግ ጥሩ ስሜት እንዲሰማዎ ማድረግ ይችላሉ።

● የፐሬድ መምጣት ምልክቶች እንደጀመሩ ወዲያውኑ እንደ ዲክሎፌናክ የመሳሰሉ የህመም ማስታገሻ ክኒኖችን መዋጥ ይጀምሩ። ከዚያም 2 ወይም ለ 3 ቀናት መውሰድዎን ይቀጥሉ።

● በታችኛው የሆድዎ አከባቢ ላይ የሞቀ ፓድን ወይም ሙቅ ውሃ የያዘ ጠርሙ ያድርጉ

● በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ

ዶክተር ወይም ነርስ ማየት አለብኝ?

ከስር የተዘረዘሩት ምልክቶች ከታዩብዎ ሐኪምዎን ወይም ነርስዎን ያማክሩ

● ህመሙ እየባሰ ከመጣ

● ህመሙ የህመም ማስታገሻ መድኃኒት ካላስታገሰው

● ህመሙ ከፐሬድ ውጪ የሚቀጥል ከሆነ

ላደርጋቸው የሚገባኝ ምርመራዎች አሉን?

የርስዎ እድሜ ፣ ሌሎች ተጨማሪ ምልክቶች እና ግለሰባዊ ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ ምንአይነት ምርመራ ማድረግ እንዳለብዎት ሐኪምዎ ወይም ነርስ ይወስናሉ።

አብዛኛዎቹ ሴቶች የአካል ምርመራ ብቻ ያስፈልጋቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ግን ተጨማሪ ምርመራዎች ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ለምሳሌ ፦

● የማህጸን አልትራሳውንድ

● የአባላዘር በሽታዎች ምርመራ እና

● ላፓሮስኮፒ

ከሚያስፈልጉ ምርመራዎች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።

የፐሬድ ህመም ህክምናው ምንድን ነው ?

ህክምናው በመንስኤው ላይ የተመሰረተ ነው። በጣም የተለመዱት ሕክምናዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላል።

● የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች

● የወሊድ መከላከያ ክኒን ወይም ሌላ ዓይነት የወሊድ መቆጣጠሪያዎችን (ሆርሞኖችን) ያጠቃልላል

በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ጠቃሚ ጽሁፎች ለማንበብ ገፃችን "ላይክ" ያድርጉ::

ስልምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች መረጃ ለማግኘት በ 0961999109 ይደውሉ::
ሀበሻ የጽንስና የማህጸን ልዩ ክሊኒክ
አድራሻ:- ጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ላመርገየር ሆቴል ጀርባ
ስልክ ቁጥር 0961999109
ጎንደር ኢትዮጵያ

Address

Gondar

Opening Hours

Monday 12:00 - 14:00
Wednesday 12:00 - 14:00
Friday 12:00 - 14:00
Saturday 12:00 - 14:00

Telephone

+251913091603

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr.Solomon, MFM ዶ/ር ሰለሞን ልዮ የነፍሰጡር እናቶች ህክምና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr.Solomon, MFM ዶ/ር ሰለሞን ልዮ የነፍሰጡር እናቶች ህክምና:

Share