31/05/2022
የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) ምልክቶች
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ምልክቶች ከፈንጣጣ (small pox) ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም የበሽታው ምልክቶች በተወሰነ ቀለል ያለ ነው።.
በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ አንድ ሰው ከተያዘ በኋላ ፡ የበሽታው ምልክቶች ለመታየት ከ7-14 ቀናት ይወስዳል።
ታካሚው መጀመሪያ የሚታይባቸው ምልክቶች፡• ትኩሳት፡ ራስ ምታት፡የጡንቻ ህመም ፡የጀርባ ህመም ፡ድካም ፡ብርድ ብርድ ማለት እና የንፍፊት መቆጣት (lymphadenopathy) ነው።
ትኩሳት ከተከሰተ፡በአማካኝ ከ1 እስከ 3 ቀናት በኋላ ፤ በፊት፡በእጅ መዳፎች ፡በእግር መርገጫ ፡ አፍ ፡ዓይን ላይ ሽፍታ ይታያል ።
ሽፍታው መጀመሪያ ቀላ ቀላ ያለ መልክ መቀየር፤ከዛም ከፍ ከፍ ብሎ የሚታይ ሽፍታ፤ቀጥሎም ውሀ መቐጠር እና ነጣ ያለ ፋሳሽ የቐጠረ ሽፍታ ያስከትላል።
ከ 2- 4 ሳምንታት በኋላ ሽፍታው ደርቆ ይረግፋል።
በከፋ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ሊመጡ የሚችሉ ህመሞች መሀል
• የሳንባ ምች (bronchopneumonia)
• አጠቃላይ የሰውነት (የደም) በሽታ
• የአንጎል እና የዓይን በሽታ ለሞት ሊዳርጉ ይችላሉ።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ ገዳይ ነው?
የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከተያዘ አስር ሰው መሀል በአንዱ ላይ ሞት ያስከትላል።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መያዞን እንዴት ማወቅ ይቻላል?
የህክምና ታሪክ (የጉዞ ታሪክ, የዝንጀሮ ፈንጣጣ ካላቸው ሰዎች ጋር መኖር፤በሽታው ባለበት እንስሳት ንክሻ ወይም ጭረት ካጋጠሞ ፡በበሽታው የተያዘ በከፊል የበሰለ ወይም ጥሬ ስጋ ከበሉ ወ።ዘ።ተ)
• የቤተሙከራ ፍተሻዎች ፡ከቆዳ ቁስለት በሚወሰድ የዘረምል ምርመራ(PCR)
• የስነደዌ ምርመራ፡ ትንሽ ከቆዳ ላይ ተቆርጦ በሚወሰድ ምርመራ።
ቫይረሱ በደም ውስጥ ለአጭር ጊዜ ብቻ ስለሚቆይ ፤በሽታው መኖሩን ለማወቅ የደም ምርመራ ብዙውን ጊዜ ተመራጭ አይደለም።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ እንዴት ነው የሚታከመው?
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በአሁኑ ጊዜ ምንም ህክምና የለውም። ይሁን እንጂ, ከላይ እንደተጠቀሰው 90% ሰው ከበሽታው በራሱ ይድናል።
የበሽታውን መስፋፋት እና ክፋት ለመቆጣጠር ከሚረዱ መድሀኒቶች መካከል፡
• የፈንጣጣ ክትባት
• የፈንጣጣ በሽታ የሚከላከል ፕሮቲን (VIG) እና ፀረ-ቫይረስ መድሃኒቶች አሉ።
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መረጃ ፤ የፈንጣጣ ክትባት በአማካይ 85 በመቶ የዝንጀሮ ፈንጣጣን የመከላከል አቅም ኣለው።