Dr Timothy

Dr  Timothy I'm here to make the difference

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ በማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ ሕንጻ ላይ ድንገት ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በማህበራዊ...
03/09/2026

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ በማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ ሕንጻ ላይ ድንገት ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ ሕንጻ ላይ ዛሬ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም መንስኤው ያልታወቀ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

የእሳት አደጋው በአሁን ሰዓት በዪኒቨርሲቲውና በአካባቢው ማህበረሰብ ብርቱ ትግል በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው እና የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የሶዶ ከተማ እና የዞን አስተዳደር አካላት ላደረጉት ብርቱ ትብብርና ርብርብ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ከልብ የመነጨ ምስጋና ያቀርባል።

የደረሰው የእሳት አደጋ የከፋ እንዳይሆን መላው ማህበረሰብና የግል ድርቶች ሁሉ ላደረጋችሁት ሁሉአቀፍ ትብብር የዩኒቨርስቲው አስተዳደር በድጋሚ ያመሰግናል።

የእሳት አደጋው መንስዔና የጉዳቱን መጠን በሚመለከተው አካል ተጣርቶ ሲቀርብ ለማህበረሰቡ መረጃ የሚንሰጥ ይሆናል።

ሹመቶች  ክፍል 4Part 1,2 & 3 ቀድሞ ስለተለቀቀ አስቀድመው ያንብቡ !!!ይህ አገልግሎት ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን ያስፈልጋል?ታዲያ የክርስቶስ ሐዋርያነት ማዕረግ ካበቃ፣ ይህ የአብያተ ክር...
04/06/2026

ሹመቶች
ክፍል 4

Part 1,2 & 3 ቀድሞ ስለተለቀቀ አስቀድመው ያንብቡ !!!

ይህ አገልግሎት ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን ያስፈልጋል?

ታዲያ የክርስቶስ ሐዋርያነት ማዕረግ ካበቃ፣ ይህ የአብያተ ክርስቲያናት መልእክተኝነት (Missionary Function) ዛሬ ላለችው የአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ያስፈልጋል የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት። መልሱ አዎ፣ ዛሬም እጅግ በጣም ያስፈልጋል የቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ሀብትም ነው። ዛሬ ባለው አውድ እኛ እነዚህን ወገኖች የምንጠራቸው የወንጌል አቅኚዎች ወይም ሚስዮናውያን (Missionaries) በማለት ሲሆን፣ ይህ የላቲን ቃል (Missio) ቀጥተኛ ትርጉሙም ልክ እንደ ግሪክኛው አፖስቶሎስ የተላከ ማለት ነው። ማቴ 28:19 ላይ የተሰጠው ታላቁ የተልዕኮ ትእዛዝ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የማይቆም በመሆኑ፣ ወንጌል ባልደረሰበት ሥፍራ ሁሉ ሄደው፣ ሕይወታቸውን ሰጥተው፣ አዳዲስ ነፍሳትን ማርከው ቤተ ክርስቲያን የሚተክሉ ተንቀሳቃሽ መልእክተኞች ዛሬም ለቤተ ክርስቲያን እጅግ አስገዳጅ ፍላጎቶች ናቸው። እግዚአብሔር በእነዚህ ታማኝ የሚስዮን መልእክተኞች አማካኝነት ዛሬም በሰፊው ይሠራል፣ ድንቅና ተአምራትን ያደርጋል፣ የክርስቶስንም አካል ያንጻል።

ነገር ግን በመካከላችው ያለው ትልቁና ሊሰመርበት የሚገባው ልዩነት መጽሐፍ ቅዱሳዊው የሚስዮን አገልግሎት (Missionary Function) ዛሬም በኃይል የሚቀጥል ሲሆን፣ በአንድ ቦታ ተዘርግቶ በሰው ላይ የሚነግሥ፣ ማዕረግ ጭኖ የሚቀመጥና አዲስ ትእዛዝ የሚሰጥ መዋቅራዊ የሐዋርያነት ሹመት (Office) ግን ሙሉ በሙሉ ያበቃ መሆኑ ነው። ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ያለው መዋቅር በ1 ጢሞቴዎስ 3 አና በኤፌ 4:11 ላይ እንደተቀመጠው የወንጌል ሚስዮናውያን ተግባር፣ የአጥቢያ መጋቢዎች ፣ አስተማሪዎችና የዲያቆናት አገልግሎትና የመሳሰሉት ብቻ ናቸው ።

በክፍል 5 1ቆሮ 12:28 እና ኤፌ 4:11-12 ያለውን አከራካሪ ሀሳብ ባጭሩ እናነሳና የሐዋርያት ሹመት ጉዳይ እንጨርሰዋለን ......part 5....

ሹመቶች ክፍል 3ከዝህ ቀደም የተለቀቁትን ክፍል 1&2 አስቀድመው ያንብቡት የአብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያት (Apostles of the Churches)በቀደሙት ክፍሎቻችን በቀጥታ ከክርስቶስ መለ...
04/06/2026

ሹመቶች

ክፍል 3

ከዝህ ቀደም የተለቀቁትን ክፍል 1&2 አስቀድመው ያንብቡት

የአብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያት (Apostles of the Churches)

በቀደሙት ክፍሎቻችን በቀጥታ ከክርስቶስ መለኮታዊ ሥልጣን የተቀበሉትና የቤተ ክርስቲያንን መሠረት የጣሉት የክርስቶስ ሐዋርያት መዋቅራዊ ሹመት መዘጋቱን በግልጽ አይተናል። አሁን ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ''የአብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያት'' ወይም በግሪክኛው (Apostoloi Ekklesiōn) ስለሚላቸው አገልጋዮች ይበልጥ በሰፊውና በጥልቀት ማየት ይኖርብናል። ሐዋርያው ጳውሎስ በ 2ቆሮ 8:23 ላይ ስለ አብረውት ስላሉት ወንድሞች ሲናገር ''እነርሱ የአብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያት (መልእክተኞች) ናቸው'' በማለት በግልጽ ይጠራቸዋል። እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባው ታላቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት አለ፤ እሱም ይህ አገላለጽ የሥልጣን ማዕረግን ወይም ራሱን የቻለ መዋቅራዊ ሹመትን (Office) ሳይሆን የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን ውክልና ይዞ የመሄድን የተግባር አገልግሎት (Function) ብቻ የሚያሳይ መሆኑን ነው። እነዚህ ወገኞች የጥሪአቸው ምንጭ በቀጥታ ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የተገኘ ሲሆን፣ ተግባራቸውም ከአንድ ቦታ ተነስተው ወንጌልን ለመስበክ፣ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን ለመትከል ወይም የቅዱሳንን እርዳታና መልእክት ይዞ ለመጓዝ የተላኩ ታማኝ ተላላኪዎች መሆን ነበር።

ለዚህም ነው በፊልጵ 2:25 ላይ ጳውሎስ ስለ አፍሮዲጡ ሲናገር የእናንተ ሐዋርያ ወይም መልእክተኛ ይለዋል። አፍሮዲጡ የፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያን ለጳውሎስ እርዳታ እንድታደርስ የላከችው ታማኝ ተላላኪ እንጂ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የጻፈ ወይም በአማኞች ላይ ፍጹም የበላይ ሥልጣን ያለው መዋቅራዊ ሹም አልነበረም። ስለዚህ የአብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያት ማለት በቃሉ ቀጥተኛ ፍቺ መሠረት የቤተ ክርስቲያን የልዑክ ተላላኪዎች (Church Messengers) ማለት እንጂ የሥልጣን ባለቤቶች አይደሉም።

ይህንን እውነት ይበልጥ በሰፊው ለመረዳት በሐዋርያት ሥራ 13:1-3 ያለውን ታሪካዊ ክስተት ማየት እንችላለን። በአንጾኪያ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነቢያትና መምህራን በጸምና በጸሎት ጌታን በሚያመልኩበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በርናባስንና ሳውልን ለጠራቸው ሥራ እንዲለዩአቸው ተናገረ። በዚያን ጊዜ የነበሩት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከጸለዩና እጃቸውን በላያቸው ላይ ከጫኑ በኋላ አሰናበቷቸው ወይም ላኳቸው። እዚህ ጋ በርናባስና ጳውሎስ ሐዋርያዊ አገልግሎት የጀመሩት በራሳቸው ሥልጣን ሳይሆን በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እውቅናና ላኪነት መሆኑን እንረዳለን። ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓት በአዲስ ኪዳን ውስጥ የአገልግሎት ስምሪት እንዴት እንደሚከናወን ፍጹም ማሳያ ነው። እግዚአብሔር ሰዎችን በሉዓላዊ ፈቃዱ ለወንጌል ሥራ ቢጠራቸውም፣ ጥሪአቸው ግን በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መዋቅርና ጸሎት ውስጥ አልፎ የሚላክ ተግባራዊ አገልግሎት እንጂ፣ ራሳቸውን በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚሾሙበት የክብር ማዕረግ አልነበረም።
በቤተክርስቲያን ሐዋርያት ላይ እንቀጥላለን .......part 4......

Part 2 ከዚህ ቀደሞ የተለቀቀውን part 1 አስቀድመው ያንብቡት ሹመቶች (office )1.ሐዋርያት (Apostleship) እውነተኛው የሐዋርያነት መመዘኛ የግሪክ ቃል «አፖስቶሎስ» ተላላኪ...
01/06/2026

Part 2
ከዚህ ቀደሞ የተለቀቀውን part 1 አስቀድመው ያንብቡት

ሹመቶች (office )

1.ሐዋርያት (Apostleship)

እውነተኛው የሐዋርያነት መመዘኛ

የግሪክ ቃል «አፖስቶሎስ» ተላላኪነትን የሚያሳይ ቢሆንም፣ የክርስቶስ ቀጥተኛ ሐዋርያ ለመሆን መጽሐፍ ቅዱስ ፈጽሞ የማይታለፉ ታሪካዊ መመዘኛዎችን ያስቀምጣል። በሐዋርያት ሥራ 1:21-22 ላይ እንደተጻፈው በይሁዳ ምትክ ሌላ ሰው ለመተካት በጸሎት በተሰበሰቡ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ያስቀመጠው መስፈርት ጌታ ኢየሱስ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ እስከ እርገቱ ድረስ በመካከላቸው በነበረበት ዘመን ሁሉ አብሮ የተጓዘና ከሁሉም በላይ ደግሞ «የትንሣኤው የአይን ምስክር» የሆነ ሰው ብቻ ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስም ቢሆን ከ12ቱ ቁጥር ውጭ በልዩ ሁኔታ የተጠራ ቢሆንም፣ የሐዋርያነት ሥልጣኑን ለማስከበር የተከራከረው ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በደማስቆ መንገድ ላይ በአይን ስላየውና በቀጥታ ከእርሱ መመሪያ ስለተቀበለ ነው (1ቆሮ 9:1፣ ገላ 1:1)። ይህ የሚያሳየው የክርስቶስ ሐዋርያ መሆን ዝም ብሎ በራእይ ወይም በህልም የሚገኝ ሳይሆን፣ ከሙታን የተነሳውን ታሪካዊውን ክርስቶስን በአካል ከማየት ጋር በጥብቅ የተያዘ ልዩ ጥሪ መሆኑን ነው።

ይህ ታሪካዊ ጥሪ በእርሱ ማለፍ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን ጳውሎስ ራሱ በ1ቆሮ 15:8 ላይ ''ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ'' በማለት ያረጋግጣል። እዚህ ጋ ''ከሁሉም በኋላ'' ለመግለጽ የተጠቀመበት የግሪክ ቃል (Eschaton) የሚል ሲሆን፣ ትርጉሙም በአንድ ቅደም ተከተል ውስጥ የመጨረሻው ማቆሚያ ወይም ከእሱ በኋላ ሌላ ምንም የማይከተልበት ፍጹም ማጠቃለያ መስመር ማለት ነው። ጳውሎስ ይህንን ቃል የተጠቀመው የትንሣኤው ጌታ በአካል ተገልጦ ሐዋርያ የማድረጉ ሂደት በእርሱ ላይ ማኅተም ማግኘቱን ለማወጅ ነው።

በኤፌ 2:20 ላይ እንደተጻፈው ሐዋርያት የቤተ ክርስቲያን ''መሠረት ጣዮች'' ናቸው፤ መሠረት ደግሞ በሕንፃ ግንባታ ታሪክ አንድ ጊዜ ተጥሎ የሚያበቃ እንጂ ሁልጊዜ የሚጣል አይደለም። እንዲሁም በራእይ 21:14 ላይ የሰማያዊቷን ኢየሩሳሌም ቅጥር ሲገልጥ ከተማዪቱ አሥራ ሁለት መሠረቶች እንደነበሩትና በእነርሱም ውስጥ የበጉ አሥራ ሁለት ሐዋርያት ስሞች ብቻ እንደተጻፉ ይናገራል። ዛሬ ከሙታን የተነሳውን ክርስቶስን በዚያ ታሪካዊ መንገድ በአይን ያየ ሰው ስለሌለና መሠረቱም ተጥሎ ስላለቀ የክርስቶስ ሐዋርያነት ሹመት ሙሉ በሙሉ አብቅቷል። የክርስቶስ የምለው ቃል ይሰመርበት ። እና የቤተ ክርስቲያን የተባሉትስ እንድሁም ለሎችም የክርስቶስ ተብለዋል እነሱስ የምለውን እንቀጥላለን ........

Part - 1የሁከቱ ሁሉ ምንጭ አስቀድሞ ማንነታቸው በግልጽ ሳይብራራ ወደ ውግዘት መገባቱ ስለመሰለኝ እስት እያንዳንዳቸው ምንድናቸው ምለውን እንመልከት ሹመቶች (Office) 1.ሐዋርያነት (...
01/06/2026

Part - 1
የሁከቱ ሁሉ ምንጭ አስቀድሞ ማንነታቸው በግልጽ ሳይብራራ ወደ ውግዘት መገባቱ ስለመሰለኝ እስት እያንዳንዳቸው ምንድናቸው ምለውን እንመልከት

ሹመቶች (Office)

1.ሐዋርያነት (Apostleship)

«ሐዋርያ» የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን የተጻፈበት ዋናው የግሪክ ቃል (Apostolos) ይባላል። ይህ ቃል የመጣው (Apostellō) ከሚለው ግስ ሲሆን፣ ትርጉሙም «ለልዩ ተልዕኮ ወደ ሌላ ቦታ እልካለሁ» ማለት ነው። በጥንቷ ግሪክ አንድ ንጉሥ ወይም የጦር መሪ የተለየ ትእዛዝ ይዞ እንዲሄድ በይፋ የሚልከው ሙሉ ሥልጣን ያለው ልዑክ «አፖስቶሎስ» ይባል ነበር።

በዚህ መዋቅር ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የመጀመሪያውና ዋናው ሐዋርያ አድርጎ ያቀርበዋል። በዕብ 3:1 ላይ «የእምነታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ» ተብሎ እንደተጻፈው፣ ኢየሱስ የአብን ፈቃድና መለኮታዊ ትእዛዝ ሙሉ ሥልጣን ይዞ ወደ ምድር ለመፈጸም የመጣ ፍጹም የሰማይ ልዑክ (ዮሐ 5:30፣ 17:18) ነው። እርሱ ደግሞ በተራው የእርሱን መለኮታዊ መንግሥት ወኪሎች እንዲሆኑ ደቀ መዛሙርቱን መርጦ «ሐዋርያት» ብሎ ሰየማቸው (ሉቃ 6:13)።

በአዲስ ኪዳን ሰዋስው ውስጥ ይህ «አፖስቶሎስ» የሚለው ቃል ከባለቤትነት ስም (Genitive Case) ጋር ተያይዞ ሲገባ የሹመቱን ደረጃና ምንጭ ለይቶ ያሳያል። ሐዋርያው ጳውሎስና ጴጥሮስ በደብዳቤዎቻቸው መግቢያ ላይ ራሳቸውን «የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ» ወይም እያሉ ይጠራሉ። (1ቆሮ 1:1እና 1ጴጥ 1:1)። ይህ አገላለጽ ላኪያቸውና የሥልጣናቸው ምንጭ በቀጥታ ራሱ ክርስቶስ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ ይህ ደረጃ ያላቸው ሐዋርያት የቤተ ክ/ንን መሠረት የጣሉና የእግዚአብሔርን መለኮታዊ መገለጥ አዲስ ኪዳንን የመጻፍ ፍጹም ሥልጣን የተሰጣቸው ነበሩ።
በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ በርናባስና ስለ ሌሎች ወንድሞች ሲናገር «የአብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያት» በማለት የላኪያቸውን ምንጭ ይቀይረዋል (2ቆሮ 8:23)። እነዚህ ወገኞች የሥልጣን ምንጫቸው አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ስለሆነች፣ የተሰጣቸው ተልዕኮም ወንጌልንና እርዳታን ይዞ ከአገር አገር መዞር እንጂ በቤተ ክ/ን ላይ አዲስ ሕግ ማውጣት ወይም መዋቅራዊ ሥልጣን መያዝ አልነበረም።

ስለዚህ የቃሉ ስርወ-ፍቺ የሚያሳየን «ሐዋርያ» ማለት ተላላኪና የላኪውን መልእክት ብቻ የሚያደርስ ታማኝ ወኪል ማለት እንጂ፣ ዛሬ አንዳንዶች እንደሚያስቡት በአንድ ቦታ ተቀምጦ በሰው ላይ የሚነግሥ የሥልጣንና የክብር ሹመት አይደለም።

በዝህ office ክፍል ሁለት ይጠብቁ

🚨 ሰበር እና ልብ ሰባሪ | የሞራል ኪሳራችን ማሳያ፡ ለ35 ዓመታት ሀገር ያገለገሉት አንጋፋ ባለሙያ በአደባባይ ተደበደቡ!ይህ የአሁኑ ትውልድ ምን ያህል የሞራል፣ የስነምግባር እና የግብረገብ...
11/04/2026

🚨 ሰበር እና ልብ ሰባሪ | የሞራል ኪሳራችን ማሳያ፡ ለ35 ዓመታት ሀገር ያገለገሉት አንጋፋ ባለሙያ በአደባባይ ተደበደቡ!
ይህ የአሁኑ ትውልድ ምን ያህል የሞራል፣ የስነምግባር እና የግብረገብነት ክሳራ ውስጥ እንደገባ የሚያሳይ እጅግ አሳዛኝ እና ፀያፍ ድርጊት ተፈፅሟል። የዚህ ልብ ሰባሪ ክስተት ሰለባ የሆኑት አቶ ዋቆ ከዲር የተባሉ አንጋፋ የጤና ባለሙያ ናቸው። እኚህ የዕድሜ ባለፀጋ አገልግሎታቸውን በክብር አጠናቀው የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር ሰነዶቻቸውን በማደራጀት ላይ እያሉ፣ በባሌ ሮቤ ከተማ መናኸሪያ ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ወጣቶች አሰቃቂ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል።
አቶ ዋቆ ከዲር ለ35 ተከታታይ ዓመታት በቄለም ወለጋ ሆስፒታል፣ በጎባ ሆስፒታል፣ በጊኒር ሆስፒታል እና በራይቱ ጤና ጣቢያ ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የቆዩ ውድ የሀገር ባለውለታ ናቸው። ህይወት አድነው፣ በሽተኛ አስታመው እና ሀገርን በታማኝነት አገልግለው ለጡረታ ሲበቁ፤ የህይወት ዘመን ድካማቸው ሽልማት በአደባባይ መደብደብ እና መዋረድ መሆኑ የደረስንበትን የህሊና መሞት ፍንትው አድርጎ ያሳያል።
ይህንን ዘግናኝ ድርጊት የፈፀሙት ወጣቶች ከሌላ ፕላኔት የመጡ ሳይሆኑ፣ የዚሁ ማህበረሰብ እና ስርዓት ውጤቶች ናቸው። ህግ በማይከበርበት ማህበረሰብ ውስጥ ህግ የማያከብር ትውልድ መፈጠሩ የፀሀይ ብርሃን ያህል ግልፅ ነው። የሞራልና የስነምግባር ተቋማት የራሳቸውን ኃላፊነት መወጣት ሲያቅታቸው፤ ጨካኝ፣ ለማንም የማይገደው፣ እጅግ ራስ ወዳድ እና የሞራል ስብእና የጎደለው አመፀኛ ትውልድ መፈጠሩ የማይቀር እውነት ነው።
ለዚህ አሳሳቢ የትውልድ ውድቀት ደግሞ ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ መሪዎች እና የሃይማኖት አባቶች በሙሉ ተጠያቂዎች ናቸው። በጥቂት መልካም ሰዎች ብንፅናናም፣ ከአገር ጫፍ እስከ ጫፍ እየታየ እና እየተሰማ ያለው የሞራል ስብራት ግን ሀገርን ወደ ባሰ አዘቅት ከመክተቱ በፊት ሁላችንንም ሊያነቃን ይገባል።

A Message for 🇪🇹Ethiopia 🐕 What Morocco’s Stray Dog Crisis Teaches EthiopiaRecently, Morocco has faced global outrage ov...
21/02/2026

A Message for 🇪🇹Ethiopia

🐕 What Morocco’s Stray Dog Crisis Teaches Ethiopia

Recently, Morocco has faced global outrage over reports of mass killing of stray dogs, allegedly linked to preparations for the 2030 World Cup.

Even though no court has punished Morocco yet, the country is already paying a serious price.

🌍 What consequences can a country face for mass dog killings?

❌ International shame and reputation damage

Countries accused of animal cruelty lose global respect. Media, NGOs, and the public label them as inhumane.

❌ Tourism and economic loss
Tourists avoid countries

associated with cruelty. Campaigns and boycotts reduce income and investment.

❌ Pressure from global institutions

Organizations like FIFA, the EU, and the UN may apply monitoring, conditions, or restrictions.

❌ Public anger and activism
International attention

strengthens local activists and increases internal pressure on governments.

📚 Lessons from Other Countries

Romania faced years of EU criticism after killing stray dogs. The problem only improved after switching to sterilization.

Brazil was forced to change its methods due to global pressure before major sports events.

Countries that continued killing failed to control rabies.

Countries that vaccinated and sterilized dogs succeeded.

🚨 The Scientific Truth (WHO)
Rabies cannot be controlled by killing dogs.

It is controlled by vaccinating at least 70% of the dog population and using sterilization and community education.

Mass killing: ❌ Does not stop rabies

❌ Makes the problem worse

❌ Damages a country’s image

🇪🇹 A Message for Ethiopia

What is happening in Morocco shows us one clear truth:

👉 Cruelty is no longer a “local issue.” The world is watching.

If Ethiopia continues mass poisoning and killing of dogs:The same international backlash will come.

Public health will not improve.

Our country’s image will suffer.

Humane solutions are not weakness.

They are intelligence, science, and responsibility.

📢

09/09/2025
Timothy brand shoes 0949781509Inbox me
15/08/2025

Timothy brand shoes 0949781509
Inbox me

Check out ’s video.

Address

Wolaita S**o
S**o

Telephone

+251949781509

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Timothy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr Timothy:

Shortcuts

Share

Category