United Road

Directions Website

United Road Sex partner

Congrates United Family
25/08/2026

Congrates United Family

15/12/2025

24/08/2025
Coming Home
24/08/2025

Coming Home

🚨🚨 𝐁𝐑𝐄𝐀𝐊𝐈𝐍𝐆: Manchester United are CLOSE to signing SENNE LAMMENS! Almost there. 👀

amazing
16/07/2017

amazing

🌕🌕🌕 ኑ አብረን እንሙት 🌕🌕🌕 ገራሚ ግጥም !!!

© ከናቲ ቪሎፒያ (ጋዜጠኛ ፣ ፀሃፊ እና ክሬቲቭ ዲዛይነር)

✍ ወንጌለ አርሴናል - ወንጌለ ማንቺስተር
ትንቢተ ቢዮንሴ - መፅሃፈ ቬንገር
ትምህርተ ሞሪኖህ - ህግጋተ ክላምፕ
መልእክተ ጄዚ - ሰቆቃወ ትራምፕ
ኦሪት ዘ አሜሪካ - ኦሪት ዘ ሆሊውድ
ምፅአተ እስራኤል - ትንቢተ ቦሊውድ
ራእየ ማዶና - መልእክተ ባይበር
ኦሪት ዘ ኦባማ - ወንጌለ መ'ሸበር
ምስጢረ ሮናልዶ - ዜና ባርሴሎና
ሆኗል ይህ ዘመን ... ጌታችን ሆይ ና ና !

🌕 እስኪ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ እንደ አሳ ኖሮ - ሲሙልጨለጭ ከርሞ
በዘመን ፌርማታ - ሲሽከረከር ከስሞ
አቋም እና አቅም - የለውም አትግፋው
በብልት ማሰቢያው - ለፅናት አታልፋው
ዋ ...
ተወው ይሙትበት - ኖረህ አታኑረው
የእስስት አመሉን - ደርሰህ ላትቀይረው !

🌕 እስኪ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ ትዳር እና አዳር - በዝተው በመንደሩ
ተጋብተው ሲያበቁ - ተፋተው ለሚያድሩ
በልጆች ሜዳ ላይ - ፍ ...ቅርን አንጥፈው
ለፀብ ተማምለው - ለእርቁ ተኳርፈው
መኖርን ለሞቱት - ለነዛ ምስኪኖች
የዛሬ ትዳሮች - የነገ ጊንጥሎች
ዋ ...
ተዋቸው ይሙቱ - አታብዛ ማስማማት
ወትሮም ሊፋቱ ነው - ማግባትን ያገቧት!

🌕 እስኪ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ ለዚህ ብኩን ትውልድ - ፋሽን ላንጋደደው
በማበድ እርካታ - ለሚጨማለቀው
ቡቱቱ እና ኮተት - ደርቦ ገላው ላይ
የውስጡን ውጥንቅጥ - አደባባይ ሲያሳይ
በሱሪው ቀዳዳ - በውስጡም ቀዳዳ
መሸከም ላመመው - የህይወቱን ፍዳ
ዋ ...
ከአንገት በታች ሆኖ - የማሰቡ ርዝመት
"ስርአት" አትበለው - ተወው ይሙትበት !!!

🌕 እስኪ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ የሃይማኖት አባት - ተብለው ሲያበቁ
ተዋቸው ይሙቱ - ሳይሸማቀቁ
መስበክ ቀላል ሆኖ - መኖር ሲከብዳቸው
አይተን እንዳላየን - ሆነን ስንቀርባቸው
ወንጌል ቁርአኑን - ተናግረው ሲያበቁ
በዘር እና ቅጥፈት - ተባልተው አለቁ
ዋ ...
ኑሮ በዘዴ ነው - ሃይማኖትም የግል
በዝምታ እየው - አታብዛ ግልግል
ተዋቸው ይሙቱ - ፍቅርን እ'ያጣሉ
መሬት ሲኦል በዝቷል - ሄደው ይካፈሉ !

🌕 እስኪ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ በተግባር ሜዳ ላይ - ለሚሰወርብህ
መንፃትን ቆሽሾ - ለሚደሰኩርህ
ማመንን አንብቦ - አንተን ለሚመክርህ
ለዚህ ዘመን ምሁር - የሃይማኖት መሪ
ጥያቄ ማብዛት ነው - ትልቁ አስተማሪ !
ዋ ...
ጠይቀው ጠይቀው - መንፈሱ እስኪጨንቀው
ያልኖረበት ህይወት - እስኪያጨማልቀው
አንብቦ እንዳይመልስ - የንባብ ጋጋታ
የጥያቄውን መልስ - ከምግባሩ ፍታ !

🌕 ኑ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ በሶሻል ሚዲያው - መክሸፍ በበዛበት
የማንነት በሮች - በሚከፈቱበት
የስድብ ጋጋታን - የዝቅጠት ከፍታን
የዘር ጥንባጓሮን - የክፋት ሃተታን
ማንነቱን ቀብሮ - ለሚያለማምድህ
በአካል ምርጥ ሰው - ሆኖ ለኖረብህ
ዋ ...
ተወው ይኑርበት - ተወው ይሙትበት
ወትሮም ጤነኛ ነው - መንገድ የጠፋበት!

🌕እናም እልሃለሁ ..... እደግምልሃለሁ ! 🌕

✍ ወንጌለ አርሴናል - ወንጌለ ማንቺስተር
ትንቢተ ቢዮንሴ - መፅሃፈ ቬንገር
ትምህርተ ሞሪኖህ - ህግጋተ ክላምፕ
መልእክተ ጄዚ - ሰቆቃወ ትራምፕ
ኦሪት ዘ አሜሪካ - ኦሪት ዘ ሆሊውድ
ምፅአተ እስራኤል - ትንቢተ ቦሊውድ
ራእየ ማዶና - መልእክተ ባይበር
ኦሪት ዘ ኦባማ - ወንጌለ መ'ሸበር
ምስጢረ ሮናልዶ - ዜና ባርሴሎና
ሆኗል ይህ ዘመን ... ጌታችን ሆይ ና ና ....

✍ እስኪመጣ ጌታ - መምጣት ከቻለበት
አንተም በዚህ ፅና - መሆንን እይበት

ዋ ...

ከቆሻሻ ገንዳ - ነጭ ጨርቅ አጠብቅ
ለእድፋም ዘመን - ሃሰትን አታርቅ
ደግሞስ ስትነፃ - ማን ያጨበጭባል ?
የሰው ሁሉ አይን - ስህተት ላይ ይሮጣል !

🌕 .... ቢሆንም .... ቢሆንም ... 🌕

✍ በጠማማ ስሌት - ዘመንን አትለካ
ድሮም ሰካራም ነው - ዞሮበት 'ሚያሽካካ
ከእውነት ተስማማ - አድፈህ አትሳቀቅ
ቆመህ አትባላ - ሞተህ አትታረቅ !!!

♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦
© ከናቲ ቪሎፒያ 2009 ሰኔ
(ጋዜጠኛ ፣ ፀሃፊ እና ክሬቲቭ ዲዛይነር)

16/07/2017

🌕🌕🌕 ኑ አብረን እንሙት 🌕🌕🌕 ገራሚ ግጥም !!!

© ከናቲ ቪሎፒያ (ጋዜጠኛ ፣ ፀሃፊ እና ክሬቲቭ ዲዛይነር)

✍ ወንጌለ አርሴናል - ወንጌለ ማንቺስተር
ትንቢተ ቢዮንሴ - መፅሃፈ ቬንገር
ትምህርተ ሞሪኖህ - ህግጋተ ክላምፕ
መልእክተ ጄዚ - ሰቆቃወ ትራምፕ
ኦሪት ዘ አሜሪካ - ኦሪት ዘ ሆሊውድ
ምፅአተ እስራኤል - ትንቢተ ቦሊውድ
ራእየ ማዶና - መልእክተ ባይበር
ኦሪት ዘ ኦባማ - ወንጌለ መ'ሸበር
ምስጢረ ሮናልዶ - ዜና ባርሴሎና
ሆኗል ይህ ዘመን ... ጌታችን ሆይ ና ና !

🌕 እስኪ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ እንደ አሳ ኖሮ - ሲሙልጨለጭ ከርሞ
በዘመን ፌርማታ - ሲሽከረከር ከስሞ
አቋም እና አቅም - የለውም አትግፋው
በብልት ማሰቢያው - ለፅናት አታልፋው
ዋ ...
ተወው ይሙትበት - ኖረህ አታኑረው
የእስስት አመሉን - ደርሰህ ላትቀይረው !

🌕 እስኪ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ ትዳር እና አዳር - በዝተው በመንደሩ
ተጋብተው ሲያበቁ - ተፋተው ለሚያድሩ
በልጆች ሜዳ ላይ - ፍ ...ቅርን አንጥፈው
ለፀብ ተማምለው - ለእርቁ ተኳርፈው
መኖርን ለሞቱት - ለነዛ ምስኪኖች
የዛሬ ትዳሮች - የነገ ጊንጥሎች
ዋ ...
ተዋቸው ይሙቱ - አታብዛ ማስማማት
ወትሮም ሊፋቱ ነው - ማግባትን ያገቧት!

🌕 እስኪ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ ለዚህ ብኩን ትውልድ - ፋሽን ላንጋደደው
በማበድ እርካታ - ለሚጨማለቀው
ቡቱቱ እና ኮተት - ደርቦ ገላው ላይ
የውስጡን ውጥንቅጥ - አደባባይ ሲያሳይ
በሱሪው ቀዳዳ - በውስጡም ቀዳዳ
መሸከም ላመመው - የህይወቱን ፍዳ
ዋ ...
ከአንገት በታች ሆኖ - የማሰቡ ርዝመት
"ስርአት" አትበለው - ተወው ይሙትበት !!!

🌕 እስኪ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ የሃይማኖት አባት - ተብለው ሲያበቁ
ተዋቸው ይሙቱ - ሳይሸማቀቁ
መስበክ ቀላል ሆኖ - መኖር ሲከብዳቸው
አይተን እንዳላየን - ሆነን ስንቀርባቸው
ወንጌል ቁርአኑን - ተናግረው ሲያበቁ
በዘር እና ቅጥፈት - ተባልተው አለቁ
ዋ ...
ኑሮ በዘዴ ነው - ሃይማኖትም የግል
በዝምታ እየው - አታብዛ ግልግል
ተዋቸው ይሙቱ - ፍቅርን እ'ያጣሉ
መሬት ሲኦል በዝቷል - ሄደው ይካፈሉ !

🌕 እስኪ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ በተግባር ሜዳ ላይ - ለሚሰወርብህ
መንፃትን ቆሽሾ - ለሚደሰኩርህ
ማመንን አንብቦ - አንተን ለሚመክርህ
ለዚህ ዘመን ምሁር - የሃይማኖት መሪ
ጥያቄ ማብዛት ነው - ትልቁ አስተማሪ !
ዋ ...
ጠይቀው ጠይቀው - መንፈሱ እስኪጨንቀው
ያልኖረበት ህይወት - እስኪያጨማልቀው
አንብቦ እንዳይመልስ - የንባብ ጋጋታ
የጥያቄውን መልስ - ከምግባሩ ፍታ !

🌕 ኑ አብረን እንሙት .... 🌕

✍ በሶሻል ሚዲያው - መክሸፍ በበዛበት
የማንነት በሮች - በሚከፈቱበት
የስድብ ጋጋታን - የዝቅጠት ከፍታን
የዘር ጥንባጓሮን - የክፋት ሃተታን
ማንነቱን ቀብሮ - ለሚያለማምድህ
በአካል ምርጥ ሰው - ሆኖ ለኖረብህ
ዋ ...
ተወው ይኑርበት - ተወው ይሙትበት
ወትሮም ጤነኛ ነው - መንገድ የጠፋበት!

🌕እናም እልሃለሁ ..... እደግምልሃለሁ ! 🌕

✍ ወንጌለ አርሴናል - ወንጌለ ማንቺስተር
ትንቢተ ቢዮንሴ - መፅሃፈ ቬንገር
ትምህርተ ሞሪኖህ - ህግጋተ ክላምፕ
መልእክተ ጄዚ - ሰቆቃወ ትራምፕ
ኦሪት ዘ አሜሪካ - ኦሪት ዘ ሆሊውድ
ምፅአተ እስራኤል - ትንቢተ ቦሊውድ
ራእየ ማዶና - መልእክተ ባይበር
ኦሪት ዘ ኦባማ - ወንጌለ መ'ሸበር
ምስጢረ ሮናልዶ - ዜና ባርሴሎና
ሆኗል ይህ ዘመን ... ጌታችን ሆይ ና ና ....

✍ እስኪመጣ ጌታ - መምጣት ከቻለበት
አንተም በዚህ ፅና - መሆንን እይበት

ዋ ...

ከቆሻሻ ገንዳ - ነጭ ጨርቅ አጠብቅ
ለእድፋም ዘመን - ሃሰትን አታርቅ
ደግሞስ ስትነፃ - ማን ያጨበጭባል ?
የሰው ሁሉ አይን - ስህተት ላይ ይሮጣል !

🌕 .... ቢሆንም .... ቢሆንም ... 🌕

✍ በጠማማ ስሌት - ዘመንን አትለካ
ድሮም ሰካራም ነው - ዞሮበት 'ሚያሽካካ
ከእውነት ተስማማ - አድፈህ አትሳቀቅ
ቆመህ አትባላ - ሞተህ አትታረቅ !!!

♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦
© ከናቲ ቪሎፒያ 2009 ሰኔ
(ጋዜጠኛ ፣ ፀሃፊ እና ክሬቲቭ ዲዛይነር)

16/08/2016

"የታላላቅ ሰዎች ምርጥ አባባሎች“!
#የሙሌ ቤስት ፌስቡክገጽ✍
::**::::***:::::****:::::***:::::
1.ሌላ መንገድ በመፈለግ ጊዜህን አታጥፋ መንገድ በፊትህ ነው::ተነስቶ መራመድ ያንተ ፋንታ ነው::
(ቅ/አውግሰጢኖስ“)
:
2.ልብህን ብሩህ አድርገው ዓለምን የምትመለከትበት መስኮትነውና::
(”ጆርጅ በርናርድ ሾው“)
:
4.ሕይወት ራሷን ላለመጣል ከምትቀይሳቸው አቅጣጫዎች በአንዱ ውስጥ ማለፍ የግድ ነው::
(”ዊልያም ሺክስፒር“)
:
5.“ጥሩ ወይም መጥፎ የሚባል ነገር የለም፣ አስተሳሰባችን የሚፈጥረው እንጂ::
(”ዊልያም ሺክስፒር“)
:
6.ለሌሎች ካላሰብንና የምንችለውን ካላደረግንላቸው ከደስታ ምንጮች አንዱን እንዳደረቅን እንገንዘብ::(”ሬይሊመንዊልበት“)
:
7.ብዙ ሰዎች የሚደሰቱት ራሳቸውን ለደስተኝነት ባዘጋጁት መጠን ነው::
(”አብርሃምሊንከን“)
:
8.መፍራት ያለብን ራሱን ፍራቻን ብቻ ነው::(”ፍራንክሊን ሩዝቬልት“)
:
9.ጨለማን ሲረግሙ ከመኖር አንዲት ቁራጭ ሻማመለኮሱ ይበጃል::(”ራልፍዋልደ ኢመርሰን“)
:
10.ፍርሃትህን ለራስህ በጉያህ ሸሽግ ወኔህን ግን ከሌሎችጋር ተካፈል::(”ሮበርት ሉዊስ ስቲቭንሰን“)
፡
#የትኛውን አባባል ወደዳችሁት? ሌላም ካለ ጨምሩበት✍
፡
"ቸር እንሰንብት!"
፡
❀❀••❀❀••❀❀••❀❀
፡
☞ዘወትር አዝናኝና ቁምነገር አዘል ጹሑፎችን ማግኘት ከፈለጉ ሊንኩን ተጭነው ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡
፡
https://m.facebook.com/የሙሌ-ቤስት-ፌስቡክ-ገጽ-515423681897671/?refid=17&__xt__=11.%7B%22event%22%3A%22visit_page_tab%22%2C%22user_id%22%3A100005058725207%2C%22page_id%22%3A515423681897671%7D

Address

Sha

VEV

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when United Road posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your practice to be the top-listed clinic?

Share