CARE Clinic

Call Directions Website Contact the practice

CARE Clinic Private

02/11/2026

Eebba Gammachuu Harmee Oppieeshinii Boodaa...
የደስተኛ እናት ምርቃት ከኦፕራሲዮን በኋላ ።

29/10/2026

🤔🤔🤔🤔🤔

ፓፒላሪ የታይሮይድ ካንሰር (Papillary Thyroid Cancer – PTC)ፓፒላሪ የታይሮይድ እጢ ካንሰር በጣም የተለመደው የታይሮይድ ካንሰር ዓይነት ሲሆን፣ ከሁሉም የታይሮይድ ካንሰሮች ...
28/10/2026

ፓፒላሪ የታይሮይድ ካንሰር (Papillary Thyroid Cancer – PTC)
ፓፒላሪ የታይሮይድ እጢ ካንሰር በጣም የተለመደው የታይሮይድ ካንሰር ዓይነት ሲሆን፣ ከሁሉም የታይሮይድ ካንሰሮች ውስጥ በግምት 80–85% ያህሉን ይይዛል። ከታይሮይድ እጢ ሆርሞን አመንጪ ሴሎች የሚነሳ ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ በዝግታ ያድጋል።
ዋና ዋና ነጥቦች
1. ለበሽታው የሚያጋልጡ ምክንያቶች
በልጅነት ዕድሜ ለጨረር መጋለጥ።
በቤተሰብ ውስጥ የታይሮይድ ካንሰር ታሪክ መኖር።
የተወሰኑ የጄኔቲክ ለውጦች።
2. ምልክቶች
ህመም የሌለው የአንገት የታይሮይድ እጢ እብጠት።
የአንገት ሊምፍ ኖዶች መጨመር።
በሌላ ምርመራ ወቅት በአጋጣሚ የሚገኝ የታይሮይድ እጢ እብጠት።
3. ምርመራ
የታይሮይድ እጢ አልትራሳውንድ (Ultrasound)
ናሙና ወስዶ በማይክሮስኮፕ መመርመር (FNAC)
አስፈላጊ ሲሆን የሞለኪውላር ምርመራ (Molecular Testing)።
የአንገት ሊምፍ ኖዶችን መገምገም።
4. እንዴት ይሰራጫል?
በዋነኝነት በሊምፍ ሥርዓት ወደ አንገት ሊምፍ ኖዶች ይሰራጫል። ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች መሰራጨት ግን ከዚህ ያነሰ ነው።
5. ሕክምና
ቀዶ ጥገና፦ እንደ ካንሰሩ መጠንና የስጋት ደረጃ። የታይሮይድ ክፍልን ወይም ሙሉ ታይሮይድ እጢን ማስወገድ።
ሊምፍ ኖዶችን ማስወገድ።
የሬዲዮአዮዲን ሕክምና
የታይሮይድ ሆርሞን መድኃኒት መውሰድ።
ማስታወሻ
አጠራጣሪ እጢ ሁሉ ሙሉ ታይሮይድን ማስወገድ አያስፈልገውም። የቀዶ ጥገናው ዓይነት በካንሰሩ ደረጃ ይወሰናል።
አልትራሳውንድ
Thyroglobulin እና Anti-thyroglobulin antibodies መጠን መለካት።
ቀድሞ ማወቅ፣ ተገቢ ሕክምና እና መደበኛ ክትትል ለተሻለ የሕክምና ውጤት ወሳኝ ናቸው።
#ኬርክሊኒክ 011-3663877
0915-959383
0920-551166

28/10/2026

የሐሞት ጠጠር (Gallstones) 1. ሐሞት ከረጢት ውስጥ የሚፈጠሩ ጠንካራ ቅሪቶች ናቸው።2. መንስኤዎችና የተጋላጭነት ምክንያቶችበሐሞት ውስጥ የኮሌስትሮል ወይም የቢሊሩቢን መጠን መጨመር።...
26/10/2026

የሐሞት ጠጠር (Gallstones)
1. ሐሞት ከረጢት ውስጥ የሚፈጠሩ ጠንካራ ቅሪቶች ናቸው።
2. መንስኤዎችና የተጋላጭነት ምክንያቶች
በሐሞት ውስጥ የኮሌስትሮል ወይም የቢሊሩቢን መጠን መጨመር።
የሐሞት ከረጢት በትክክል ባዶ አለመሆን።
የሴት ፆታ፣ ዕድሜ መጨመር፣ ውፍረት፣ ፈጣን የክብደት መቀነስ ና በቤተሰብ ።
3. ምልክቶች
ብዙዎች ምንም ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ።
የሆድ ህመም፣ ከቅባታማ ምግብ በኋላ።
ህመሙ ወደ ጀርባ ወይም ወደ ቀኝ ትከሻ ሊሰራጭ ይችላል።
ማቅለሽለሽና ማስታወክ።
4. Complications
የሐሞት ከረጢት እብጠት (Acute cholecystitis)።
ወደ ዋናው የሐሞት ቱቦ የሚገባ ጠጠርና የቆዳ/የዓይን ቢጫ መሆን።
የቆሽት እብጠት (Acute pancreatitis)።
የሐሞት ቱቦ ኢንፌክሽን (Cholangitis)።
5. ምርመራ
አልትራሳውንድ :የመጀመሪያ ምርጫ ምርመራ ነው።
የጉበት ምርመራና ቢሊሩቢን።
ጠጠር በዋናው የሐሞት ቱቦ ውስጥ እንዳለ ሲጠረጠር MRCP ወይም ሌሎች ምርመራዎች።
6. ሕክምና
ምልክት ካላሳየ ክትትል ብቻ ይበቃል።
ምልክት የሚያሳዩ : ቀዶ ሕክምና ዋናው መፍትሔ ነው።
የሐሞት ከረጢት እብጠት: ማስታገሻ፣ አንቲባዮቲክና ቀዶ ሕክምና።
ዋናው የሐሞት ቱቦ ጠጠር : ERCP ወይም ቀዶ ሕክምና ጠጠሩን ማስወገድ፤ አስፈላጊ ሲሆንም የሐሞት ከረጢቱን ማስወገድ።
7. አስቸኳይ ሕክምና...
ከባድና የማይቋረጥ የሆድ ህመም፣ ትኩሳት፣ የዓይን ወይም የቆዳ ቢጫ መሆን፣ ወይም ተደጋጋሚ ማስታወክ ካለ ወዲያውኑ የሕክምና እርዳታ ያስፈልጋል።
ዋና መልዕክት፦ የሐሞት ጠጠር በአልትራሳውንድ ይለያል። ምልክት ለሚያሳዩ ቀዶ ሕክምና ተመራጭ ነው።
#ኬርክሊኒክ 011-3663877

እንቅርትን በጋራ እንከላከል ።Hucuba Ofirraa HaaDhorkinu.
22/10/2026

እንቅርትን በጋራ እንከላከል ።
Hucuba Ofirraa HaaDhorkinu.

የብሽሽት እበጥ (Inguinal Hernia) 1. ትርጉም የብሽሽት እበጥ ማለት የሆድ ውስጥ አካላት፣ በተለይም የአንጀት ክፍል ወይም የሆድ ውስጥ ስብ፣ በብሽሽት አካባቢ ባለው የጡንቻ ወይም ...
22/10/2026

የብሽሽት እበጥ (Inguinal Hernia)
1. ትርጉም
የብሽሽት እበጥ ማለት የሆድ ውስጥ አካላት፣ በተለይም የአንጀት ክፍል ወይም የሆድ ውስጥ ስብ፣ በብሽሽት አካባቢ ባለው የጡንቻ ወይም የሕብረ ሕዋስ ድክመት በኩል ወደ ውጭ መውጣት ነው።
2. ዓይነቶች (Types)
I - ቀጥተኛ ያልሆነ የብሽሽት እበጥ (Indirect inguinal hernia):
ወደ የዘር ፍሬ ከረጢት (Sc***um) ሊወርድ ይችላል። ብዙ ጊዜ ከልደት ጀምሮ ከሚኖር የአካል መክፈቻ መዘጋት አለመቻል ጋር ይያያዛል።
II - ቀጥተኛ የብሽሽት እበጥ (Direct Inguinal Hernia)
3. ምልክቶች (Clinical Presentation)
በብሽሽት አካባቢ እብጠት መታየት።
ሲያስሉ፣ ከባድ ነገር ሲያነሱ ወይም ሲገፉ እብጠቱ መጨመር።
ሲተኙ እብጠቱ መቀነስ ወይም ወደ ውስጥ መግባት።
በብሽሽት አካባቢ ሕመም፣ ምቾት ማጣት ወይም የመጎተት ስሜት።
እበጡ ወደ የዘር ፍሬ ከረጢት ከወረደ።
4. ምርመራ (Diagnosis)
የአካል ምርመራ: ብዙ ጊዜ በቂ ነው።
= አልትራሳውንድ
= CT ወይም MRI: ውስብስብ ወይም የተደበቁ እበጦች ላይ።
# የሚታይ ና ወደ ውስጥ የሚመለስ እብጠት በቀጠሮ ቀዶ ጥገና።
# ወደ ውስጥ የማይመለስ እበጥ አስቸኳይ የቀዶ ሕክምና/ምርመራ።
© የደም አቅርቦት መቋረጥ (Strangulation) ከተጠረጠረ ወዲያውኑ የድንገተኛ ቀዶ ሕክምና ያስፈልገዋል ።
የቀዶ ሕክምና ዓይነቶች
በክር ቀዶ ጥገና (Open tissue repair)
ሜሽ መጠቀም።
ላፓሮስኮፒ (Laparoscopic repair) TEP ወይም TAPP ዘዴዎች።
ለሕፃናት High ligation ይደረጋል።
5. COMPLICATIONS
Incarceration: የእብጠቱ ይዘት ወደ ሆድ ውስጥ መመለስ አለመቻል።
የአንጀት መዘጋት (Intestinal obstruction):
የአንጀት ይዘት መንቀሳቀስ መቋረጥ።
Strangulation: ወደ እብጠቱ የሚሄደው የደም አቅርቦት መቋረጥ፤ ይህም የአንጀት ሕብረ ሕዋስ መሞትን ወይም መቀደድን ሊያስከትል ይችላል።
ከቀዶ ጥገና በኋላ እብጠቱ እንደገና መከሰት።
ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የብሽሽት ሕመም።
የድንገተኛ ምልክቶች...
@ ከባድ/ድንገተኛ የብሽሽት ሕመም
@ ወደ ውስጥ የማይመለስ እብጠት
@ ማስታወክ፣ የሆድ መነፋት ወይም
@ የቆዳ ቀለም መቀየር
🚨EMERGENCY🚨 የአንጀት ደም አቅርቦት መቋረጥ ከተጠረጠረ እበቱን ወደ ውስጥ ለመመለስ አይሞክሩ።
በቀዶ ጥገና ጊዜ ሊጎዱ የሚችሉ
Vas deferens፣ የዘር ፍሬ ፧ ደም ሥሮች፣ ነርቮች፣ ፊኛ ወይም አንጀት።
የአንጀት ደም አቅርቦት መቋረጥ (Strangulation) አስቸኳይ ቀዶ ሕክምና የሚያስፈልገው ሁኔታ ነው።
#ኬርክሊኒክ
011-3663877 / 0920-551166

ፕሮስቴት (Prostate) ፕሮስቴት በወንዶች ላይ ብቻ የሚገኝ፣ ከሽንት ፊኛ በታች የሚገኝ እና የሽንት ቱቦን የሚከብብ ትንሽ እጢ ነው። ዋና ተግባሩ የዘር ፈሳሽ ክፍልን ማምረት ሲሆን ይህም...
19/10/2026

ፕሮስቴት (Prostate)
ፕሮስቴት በወንዶች ላይ ብቻ የሚገኝ፣ ከሽንት ፊኛ በታች የሚገኝ እና የሽንት ቱቦን የሚከብብ ትንሽ እጢ ነው። ዋና ተግባሩ የዘር ፈሳሽ ክፍልን ማምረት ሲሆን ይህም የዘር ፍሬዎችን ለመጠበቅና ለማጓጓዝ ይረዳል።
የፕሮስቴት ዋና ዋና በሽታዎች
1. የፕሮስቴት እጢ መጨመር (BPH)
ካንሰር ያልሆነ የፕሮስቴት እጢ መጠን መጨመር ሲሆን ከእድሜ መጨመር ጋር ይበልጥ ይታያል።
ምልክቶች፦ በተደጋጋሚ መሽናት፣ በሌሊት ብዙ ጊዜ መነሳት፣ ደካማ የሽንት ፍሰት እና ሽንትን ለመጀመር መቸገር።
2. የፕሮስቴት እብጠት (Prostatitis)
የፕሮስቴት እጢ መቆጣት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ በባክቴሪያ ኢንፌክሽን ይከሰታል።
ምልክቶች፦ በዳሌ አካባቢ ህመም፣ ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል፣ ትኩሳት እና በዘር ፈሳሽ ጊዜ ህመም።
3. የፕሮስቴት ካንሰር (Prostatic CA)
በፕሮስቴት እጢ ውስጥ የሚከሰት አደገኛ የሴሎች እድገት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ምንም ምልክት ላያሳይ ይችላል።
የተጋላጭነት ሁኔታዎች፦ እድሜ መጨመር እና በቤተሰብ ውስጥ የፕሮስቴት ካንሰር ታሪክ መኖር።
ምርመራ
የሕመም ታሪክና የሐኪም ምርመራ፦ የሽንት ችግሮችን መገምገም።
PSA የደም ምርመራ፦
ከፕሮስቴት ጋር የተያያዘ አደጋን ለመገምገም ይረዳል፤ ግን ብቻውን ካንሰርን አያረጋግጥም።
የሽንት ምርመራና አልትራሳውንድ፦
እንደ ሕመሙ ሁኔታ።
MRI እና ባዮፕሲ፦
ካንሰር ሲጠረጠር።
ሕክምና
ሕክምናው በበሽታው አይነትና በከባድነቱ ይወሰናል።
በመደበኛነት ክትትል ማድረግ።
መድኃኒቶችን መጠቀም።
የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ሲኖር ተገቢ አንቲባዮቲክ መስጠት።
ፕሮስቴትን በቀዶ ሕክምና ማስወገድ።
⚠️ ሐኪም ጋር መቼ መሄድ ያስፈልጋል?
1. ፈጽሞ መሽናት ካልቻሉ።
2. ከሽንት ችግር ጋር ትኩሳት ካለ።
3. በሽንት ውስጥ ደም ከታየ።
0920-551166 / 011-3663877

   #እጅመታጠብClean Hands, Healthy Lives. Especially for Kids.
16/10/2026

#እጅመታጠብ
Clean Hands, Healthy Lives. Especially for Kids.

Address

Walisoo
Woliso

Opening Hours

Monday 08:00 - 20:00
Tuesday 08:00 - 20:00
Wednesday 08:00 - 20:00
Thursday 08:00 - 20:00
Friday 08:00 - 20:00
Saturday 08:30 - 19:30
Sunday 08:30 - 18:30

Telephone

+251920551166

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when CARE Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to CARE Clinic:

Shortcuts

Share

Nearby clinics